የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ለ2019 ዓ.ም የበጀት ዓመት በክልሉ ውስጥ ለመንገድ ጥገና እና ግንባታ ስራ የሚያገለግሉ የተለያዩ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችና ተሽከርካሪዎችን በጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡
Amhara Rural Roads Construction Agency (የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ)
ግልጽ ብሄራዊ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 03/2019 ዓ/ም
የማሽነሪ እና ተሽከርካሪ ኪራይ አገልግሎት ግዥ
የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ለ2019 ዓ.ም የበጀት ዓመት በክልሉ ውስጥ ለመንገድ ጥገና እና ግንባታ ስራ የሚያገለግሉ የተለያዩ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችና ተሽከርካሪዎችን በጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች መሠረት በማድረግ በጨረታዉ እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የጸና ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፤
- ተጫራቾች የሚጠበቅባቸውን ግብር የከፈሉ ስለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡
- የግዥው መጠን ብር 500,000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡
- በኪራይ የሚቀርቡት ተሽከርካሪዎች እና ማሽነሪዎች የፈረስ ጉልበታቸው፣ የስሪት ዘመናቸውና ሌሎች ከጨረታ ሰነዱ የተገለፁት መስፈርቶች ተማልተው መቀረብ አለባቸው፡
- በኪራይ የሚቀርቡ ተሽከርካሪና ማሽነሪዎች ኪሎ ሜትር ወይም የነዳጅ ቆጣሪው በትክክል የሚሰራ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለማሽነሪዎች የጠቅላላ ዋጋዉን 1% ሆኖ ለሌሎች ተሽከርካሪዎች ለእያንዳንዱ ብር 10,000.00 በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ብሄራዊ ባንክ እውቅና ከሰጣቸው ባንኮች ብቻ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር ብቻ/ በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ ስም በተከፈተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000013197966 ገቢ በማድረግ የባንክ ዲፖዚት ስሊፕ ኮፒውን በመያዝ ከገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 09 ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ከ30-01-2019 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 10-02-2019 ዓ.ም ዋናው መ/ቤት ባህር ዳር በአካል በመገኘት መግዛት ይችላሉ፡
- ማንኛውም ተጫራች የመጫረቻ ሰነዱን ፋይናንሻሉንና ቴክኒካል በፖስታ በማሸግ የተሟላ አድራሻ በመፃፍ በሁለት ፖስታ ኦርጅናልና ኮፒ ተብሎ ተዘጋጅቶ ከግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ ቁጥር 03 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 10/02/2019 ዓ.ም 8:00 ሰዓት ድረስ በአካል በመገኘት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኤጀንሲው የመስብሰቢያ አዳራሽ ወይም ከግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ ቁጥር 03 በ-10/-02/2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በ8:30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡
- የዋጋ መሙያ ቅፁ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለው ከጨረታው ውድድር ውጭ ይደረጋል፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058-320-55-55 ወይም 058-222-11-07 በመደወል ወይም በኤጀንሲው ደህረ ገፅ www.arrca.gov.et ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጄንሲ
✨ messages.ai_summary
Amhara Rural Roads Construction Agency seeks to rent various construction machinery and vehicles for road maintenance and construction in the region. Bidders must have a valid trade license, TIN, tax payment proof, and VAT registration if the purchase exceeds 500,000 birr.
