Tender Detail

Tender Details

  • Company የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንገዶች ባለስልጣን ዋና መ/ቤት
  • Address በምዕራብ ኦሞ ዞን ጀሙ ከተማ ፡ ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0474527941
  • Website
  • Deadline24 Oct 2026, 5:30 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500(አምስት መቶ ብር)
  • Bid Security200000(ሁለት መቶ ሺህ ብር)
  • opening dateጨረታው በ16ኛ ቀን ከጧቱ 3:00 ተዘግቶ በዕለቱ ጧት 3፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡
  • Categories Construction Machinery , Construction Machinery And Vehicles , Machinery Rental

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት መንገዶች ባለሥልጣን ዋና መ/ቤት በተለያዩ ፕሮጀክቶች እና ጥገና ጽ/ቤቶች ለሚያከናውናቸው የመንገድ ግንባታ እና ጥገና ሥራ አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ማሽነሪዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል፡፡

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንገዶች ባለስልጣን ዋና መ/ቤት


ድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር ደ/ም/መ/ባ/03/2019

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት መንገዶች ባለሥልጣን ዋና መ/ቤት በተለያዩ ፕሮጀክቶች እና ጥገና ጽ/ቤቶች ለሚያከናውናቸው የመንገድ ግንባታ እና ጥገና ሥራ አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ማሽነሪዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል፡፡

የማሽኑ ዓይነትየማሽኑ ፈረስ ጉልበትየስሪት ዘመን እ.ኤ.አየሚቀመጠው የነዳጅ ዓይነትለአንድ ማሽን የሚፈለገው ሰዓትብዛት በዲስትሪክት ቦንጋብዛት በዲስትሪክት ታርጫብዛት በዲስትሪክት ሚዛን
ዶዘር305 እና በላይ2012 እና በላይናፍጣ1200222
ኤክስካቫተር247 እና በላይ2016 እና በላይናፍጣ1200111
ሮለር140 እና በላይ2013 እና በላይናፍጣ800222

በዚሁም መሰረት ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ዝርዝር መሰረት አቅራቢዎችን ይጋብዛል፡-

  1. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችለውን የዘመኑን ግብር የተከፈለበትን ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ የንግድ ሥራ ፈቃድ ወይም የአገልግሎት ሥራ ፈቃድ፣ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ( TIN NO) እና በጨረታ ለመሳተፍ ከህገር ውስጥ ገቢ ቢሮ የድጋፍ ደብዳቤ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዞ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች ዋጋቸውን በታሸገ ኤንቬሎፕ የፋይናንሻል እና ቴክኒካል ፕሮፖዛሉን በተለያዩ ፖስታ በማድረግ አንድ ዋና እና ሁለት ኮፒ ኦርጂናል እና ኮፒ በማለት እና የጨረታ ማስከበሪያውንም ለእያንዳንዱ ሎት በተለያዩ ፖስታ ለየብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በባለሥልጣን መ/ቤቱ የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000642058936 ገቢ በማድረግ የባንክ ደረሰኙን በመያዝ ከባለስልጣን መ/ቤቱ ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ኬዝ ቲም ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  4. የጨረታ አሸናፊ የሚወሰነው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሠረት ሲሆን ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛውም አቅራቢ ክፍት ነው፡፡
  5. አቅራቢዎች ጨረታውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ገቢ የሚያደርጉበት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛ ቀን ሲሆን ጨረታው ከቀኑ 11:30 ድረስ ይሆናል፡፡ ጨረታው በ16ኛ ቀን ከጧቱ 3:00 ተዘግቶ በዕለቱ ጧት 3፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 200000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚህ ውጭ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም ፡፡
  7. ተጫራቾች በጨረታው ደንብና መመሪያ መሠረት ጨረታቸውን ማቅረብ አለባቸው ከጨረታ ደንብና መመሪያ ውጭ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም
  8. ተጫራቾች ከ2015 ዓም ጀምሮ በተመሳሳይ ዘርፍ ከሠሩበት የመንግሥት መ/ቤት ቢያንስ አንድ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዞ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  9. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ

አድራሻ: በ ምዕራብ ኦሞ ዞን ጀሙ ከተማ የሚገኘው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግሥት መንገዶች ባለሥልጣን ዋና መ/ቤት በግዢ አቅርቦትና አስተዳደር ዘርፍ ግዢ ንብረት አስተዳደር ኬዝ ቲም ቢሮ በአካል በመቅረብ ማነጋገር ወይም በስልክ ቁጥር 0474527941/0474527727 ደውለው ማነጋገር ይቻላል፡፡

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግሥት መንገዶች ባለሥልጣን ዋና መ/ቤት /ምዕራብ ኦሞ ዞን ጀሙ ኢትዮጵያ/

✨ messages.ai_summary
South West Ethiopia Peoples' Region Roads Authority seeks to rent construction machinery—bulldozers, excavators, and rollers—for road construction and maintenance projects across its district offices. Open to any supplier regardless of nationality. Bidders must submit a valid business license, supplier certificate, VAT and TIN registration, tax clearance, and a supporting letter from the Domestic Revenue Office.
Save Tender