Tender Detail

Tender Details

  • Company የወላይታ ሶዶ ከተማ ውሃና ፍሳሽ ኮርፖሬሽን
  • Address ወላይታ ሶዶ ከተማ : ደቡብ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 0465512333
  • Website
  • Deadline23 Oct 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceየማይመለስ ብር 200 /ብር ሁለት መቶ ብቻ/
  • Bid Security50,000 (ሃምሳ ሺህ) ሲፒኦ ብቻ
  • opening dateበዕለቱ 8፡30
  • Categories Water Pipes And Fittings

የHDP፣ DCI፣ CI መገጣጠሚያዎች፣ ቢ.ጋ.ቪ እና የቢ.ጋ.ቪ መገጣጠሚያ ግዥ - የወላይታ ሶዶ ከተማ ውሃና ፍሳሽ ኮርፖሬሽን

የወላይታ ሶዶ ከተማ ውሃና ፍሳሽ ኮርፖሬሽን


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ ዞን የሶዶ ከተማ ውሃና ፍሳሽ ኮርፖሬሽን በ2019 ዓ.ም የተለያዩ መጠን ያላቸው HDP መገጣጠሚያ DCI መገጣጠሚያ CI መገጣጠሚያ ቢ.ጋ.ቪ እና የቢ.ጋ.ቪ መገጣጠሚያ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ ተጫራቾች፡-

  1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ሰርተፊኬት እና የታክስ ከፋይነት ማረጋገጫ (ቲን) ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  2. የዕቃ ወይም የአገልግሎት አቅራቢነት ምስክር ወረቀት በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  3. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 200 /ብር ሁለት መቶ ብቻ/ እየከፈሉ ከወ/ሶ/ዶ ከተማ ውሃና ፍሳሽ ኮርፖሬሽን ቢሮ ቁጥር 21 የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሠነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 50,000 (ሃምሳ ሺህ) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች እንዲያንዱን ዕቃ የሚያቀርቡበትን የመወዳደሪያ ዋጋ በጨረታ ሠነዱ ላይ በተዘረዘረው ዋጋ መሙያ ሰንጠረዥ በመሙላት በታሸገ ፖስታ በማድረግ በወላይታ ሶዶ ከተማ ውሃና ፍሳሽ ኮርፖሬሽን ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዕለቱ 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወሶ ከተማ ውሃና ፍሳሽ ኮርፖሬሽን ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ጨረታው ይከፈታል፡፡
  5. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፏቸውን ዕቃዎች አስፈላጊውን ውል በመፈፀም ሙሉ በሙሉ ወ/ሶዶ ከተማ ውሃና ፍሳሽ ኮርፖሬሽን ድረስ በማቅረብ ገቢ ሲያደርጉ ክፍያ የሚፈፀም ይሆናል፡፡
  6. ጨረታ ሠነድ አቅራረቡን በተመለከተ 1 (አንድ) ኦርጅናል እና 1 (አንድ) ኮፒ ተዘጋጅቶ በጨረታ ሠነዱ በሰም በማሸግ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 046 551 23 33 / 0913 34 17 82 / 09 12 13 89 78

መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ ዞን የሶዶ ከተማ ውሃና ፍሳሽ ኮርፖሬሽን

✨ messages.ai_summary
Wolaita Sodo City Water and Sewerage Corporation seeks suppliers for HDP, DCI, CI, B.G.V pipes and B.G.V fittings. Bidders need a renewed trade license, VAT and TIN certificates, and a supplier certificate.
Save Tender