በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 9 የሚገኝ ዋና እና ሰርቪስ ቤቶች (210 ካ/ሜ) የሐራጅ ሽያጭ - የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት
በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ፍ/ቤት የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ እና የፍ/ባለዕዳ ወ/ሮ አመለወርቅ ሳዲቅ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/310176 በ28/01/2017 ዓ/ም እና የፌ/መ/ደ/በኮ/መ/ቁ/158738 በ13/05/2017 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 9 የቤት ቁጥር አዲስ የሆነ የካርታ ቁጥር ቦሌ9/17/1/10/9308/24357/01 የተመዘገበ ዋና እና ሰርቪስ ቤቶች የይዞታ ስፋት 210 ካ/ሜ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 13,229,676.60 ( አስራ ሶስት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሃያ ዘጠኝ ሺህ ስድስት መቶ ሰባ ስድስት ከ60/100) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ጥቅምት 30 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 4፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡
የሐራጅ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጎብኘት የሚችሉ ሲሆን፤እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ው አስበልጠም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም C.P.O አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +25112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
