አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ የሰጠው ብድር ባለመከፈሉ የብድር መያዣ ንብረቶቹ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
Bank of Abyssinia S.C. (አቢሲንያ ባንክ አ.ማ)
አቢሲንያ ባንክ Bank of Abyssinia
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
| ተ.ቁ | የተበዳሪው ሙሉ ስም | የመያዣ ሰጭው ስም | የንብረቱ ዓይነትና አገልግሎት | የቦታው ስፋት | የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር | ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ | የጨረታ መነሻ ዋጋ በብር | ጨረታው የሚካሄድበት ቀን | የምዝገባ ሰዓት | የጨረታ ሰዓት | ጨረታው የወጣበት ጊዜ | ጨረታው የሚከናወንበት ስፍራ |
| 1 | አቶ ቀኔ በሃይሉ ባንቴ | ተበዳሪዉ | መኖ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ | 2000 | 44/2010 | እንጅባራ ከተማ ቀበሌ 02 | 12,248,825.32 | ህዳር 09 ቀን 2019 ዓ.ም | 4:00-5:30 | 5:30-6:00 | ለመጀመሪያ ጊዜ | ንብረቱ ባለበት ቦታ |
| 2 | ወ/ሪት እህተ ምስጌ ገዳሙ | ተበዳሪዉ | ኮንዶሚኒየም መኖሪያ | 43.84 | 8.2/927/1357/15 | ደብረ ታቦር ከተማ ቀበሌ 04 መሉ ሳይት ባለ 1 መኝታ ምድር ቤት | 928,863.77 | ህዳር 02 ቀን 2019 ዓ.ም | 4:00-5:30 | 5:30-6:00 | ለሁለተኛ ጊዜ | ንብረቱ ባለበት ቦታ |
| 3 | አቶ ተስፋዬ ሙሉጌታ ሀይሌ | ተበዳሪዉ | ኮንዶሚኒየም መኖሪያ | 40.89 | 5811/18 | ጎንደር ከተማ አዘዞ ሳይት ቀበሌ 19 ባለ 1 መኝታ 3ኛ ፎቅ | 1,259,213.30 | ጥቅምት 30 ቀን 2019 ዓ.ም | 4:00-5:30 | 9:30-10:00 | ለሁለተኛ ጊዜ | ንብረቱ ባለበት ቦታ |
| 4 | አቶ ጌትነት ዳኘዉ አየነዉ | ተበዳሪዉ | መጋዘን | 542.94 | 72/2012 | እንጅባራ ከተማ ቀበሌ 01 | 7,603,361.26 | ህዳር 09 ቀን 2019 ዓ.ም | 8:00-9:30 | 9:30-10:00 | ለሁለተኛ ጊዜ | ንብረቱ ባለበት ቦታ |
| 5 | አቶ መላኩ ደማሙ ካሳ | ተበዳሪዉ | መኖሪያ | 450 | 1060/ደ/17/2 | ግልገል በለስ ከተማ ቀበሌ 02 | 1,274,400.00 | ህዳር 11 ቀን 2019 ዓ.ም | 4:00-5:30 | 5:30-6:00 | ለሁለተኛ ጊዜ | ንብረቱ ባለበት ቦታ |
| 6 | ያሬንጃ የታሸጉ መጠጦች ጅምላ ንግድ ኃ/የተ/የግ/ማህበር | አቶ ተፈራ አላምረዉ ታዬ | መኖሪያ | 280 | የቁ/መ/ሰ/መለያ ኮድ AM001010414006 | ባህር ዳር ከተማ አጼ ቴዎድሮስ ክ/ከተማ፣ ቀበሌ 1 | 26,915,670.48 | ህዳር 08 ቀን 2019 ዓ.ም | 4:00-5:30 | 5:30-6:00 | ለመጀመሪያ ጊዜ | ንብረቱ ባለበት ቦታ |
| 7 | አቶ ቀኔ በሃይሉ ባንቴ | ተበዳሪዉ | መጋዘን | 1000 | 11513/2010 | ቡሬ ከተማ ቀበሌ 02 | 11,702,353.21 | ህዳር 07 ቀን 2019 ዓ.ም | 8:00-9:300 | 9:30-10:00 | ለሁለተኛ ጊዜ | ንብረቱ ባለበት ቦታ |
| 8 | አቶ ቀኔ በሃይሉ ባንቴ | ኬቢኤዘድ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር | መጋዘን | 1000 | 16271/2013 | ቡሬ ከተማ ቀበሌ 02 | 12,173,879.34 | ህዳር 08 ቀን 2019 ዓ.ም | 4:00-5:30 | 5:30-6:00 | ለሁለተኛ ጊዜ | ንብረቱ ባለበት ቦታ |
| 9 | አቶ ቀኔ በሃይሉ ባንቴ | ኬቢኤዘድ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር | መጋዘን | 1000 | 16272/2013 | ቡሬ ከተማ ቀበሌ 02 | 11,702,353.21 | ህዳር 09 ቀን 2019 ዓ.ም | 8:00-9:30 | 9:30-10:00 | ለሁለተኛ ጊዜ | ንብረቱ ባለበት ቦታ |
አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ የሰጠው ብድር ባለመከፈሉ የብድር መያዣ ንብረቶቹ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::
በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋውን ¼ (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በአቢሲንያ ባንክ (አ.ማ) ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው ለመሳተፍ ይችላሉ::
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት/ንብረቶች መረከብ ይኖርበታል:: በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል:: በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል::
- ተበዳሪው/መያዣ ሰጪው በሐራጁ ቀንና ሰዓት በቦታው መገኘት ይችላሉ:: ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል::
- የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን ፣ እንዲሁም ስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውም ወጪዎችንም ገገር ይከፍላል:: ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሲሆን ቀሪ የሊዝ ክፍያ ገገር ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር ይዋዋላል::
- ንብረቶቹን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አሲዞ ለመጎብኘት ወይም ለማየት ይቻላል::
- በባንኩ ብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መሠረት መስፈርቱን ለሚያሟሉ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢዎች ባንኩ ከፊል ብድር ሊሰጥ ይችላል::
- ከተራ ቁጥር 1፣ 4፣ 7፣ 8፣ 9 ለተዘረዘሩት ንብረቶች አሸናፊው 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ የሚከፍል ይሆናል::
- ጨረታው የሚከናወነው በሰንጠረዡ በተመለከተው ስፍራ ነው::
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0911580063/ ወይም 09-53-84-70-04 ባህር ዳር በመደወል መጠየቅ ይቻላል::
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አቢሲንያ ባንክ የሁሉም ምርጫ! The Choice for All!
✨ messages.ai_summary
Bank of Abyssinia is selling repossessed loan-collateral properties via open auction, including a animal-feed factory, condominiums, warehouses, and residences. Bidders must deposit 25% of the starting price as a bid bond. Winners must pay in full within 15 days. The bank may offer partial loans to qualifying bidders.
Not stated in the notice: opening date, bid document price. Check the original document or ask the issuer.
