Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Agricultural Businesses Corporation (የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን)
  • Address ሳሪስ አቦ ፋፋ የምግብ አክሲዮን ጎን 200 ሜትር ገባ ብሎ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0114709095
  • Websitehttps://ethioagri.com/
  • Deadline22 Oct 2026, 4:00 PM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceየማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Bid Securityለእያንዳንዱ ንብረት: ሎት 1 እና 2 ብር 100,000.00፤ ሎት 3 ብር 50,000.00 (CPO)
  • opening dateበ 19/02/2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
  • Categories Disposal Sale , Vehicle , Construction Machinery And Vehicles

ያገለገሉ ቀላልና ከባድ ተሽከርካሪዎች፣ ተሳቢዎች፣ አውቶቢሶች፣ የእርሻ መሳሪያዎችና ዶዘሮች ሽያጭ (3 ሎቶች) - የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን

Ethiopian Agricultural Businesses Corporation (የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን)


የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን በአዲስ አበባና በቅርንጫፍ ጽ/ቤቶቹ የሚገኙ ከዚህ በታች የተገለጹትን ያገለገሉ ንብረቶችን፡-

የሎት ቁጥርየንብረቶቹ ዓይነት
ሎት- 1የተለያዩ ያገለገሉ ቀላል ተሽከርካሪዎች
ሎት- 2የተለያዩ ያገለገሉ ከባድ ተሽከርካሪዎች ፣ የከባድ ተሽከርካሪ ተሳቢዎችና አውቶቢሶች
ሎት- 3የተለያዩ ያገለገሉ የእርሻ መሳሪያዎችን፣ ዶዘሮችና ሌሎችን

በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ። ተጫራቾች

  1. ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ንብረቶቹ በሚገኙበት አዲስ አበባ ቃሊቲ መጨረሻ ባቡር ፌርማታ ጋር ሲደርሱ አዋሽ ባንክ ካለበት ህንጻ በስተጀርባ በኮርፖሬሽኑ የግብርና ምርት ማሳደጊያ አቅርቦ ዘርፍ ህንጻ 3ተኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው ፋይናንስ ገንዘብ ያዥ(ካሸር) ቢሮ እንዲሁም በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ማለትም(በአሰላ፣ በአርዳይታ፣ በኮፊሌና በሆዋሳ) በመቅረብ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  2. የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የሚካሄደው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡ ጨረታውም በ10ኛው የሥራ ቀን ማለትም በ (12/02/2019 ዓ.ም) ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ተዘግቶ የቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሰነዶች ተሰብስበው ከመጡ በኋላ በ 19/02/2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ በኢትዮጵያ የግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን የመሰባሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
  3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት ማለትም፡-

    ሎት 1፡- ላገለገሉ አነስተኛ ተሽከርካሪዎች ለእያንዳንዱ ለሚወዳደሩበት ንብረት ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር)፤

    ሎት 2፡- ለተለያዩ ያገለገሉ ከባድ ተሽከርካሪዎች፣ የከባድ ተሽከርካሪ ተሳቢዎችና አውቶቢሶች ለእያንዳንዱ ለሚወዳደሩበት ንብረት ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር)፤

    ሎት 3፡- ለተለያዩ ያገለገሉ የእርሻና ኮንስትራክሽን መሳሪያዎች እና ሌሎች ንብረቶች ለእያንዳንዳቸው ለሚወዳደሩበት ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) በኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ስም በማዘጋጀት ከጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው፡፡

  4. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ንብረት የሚገዙበትን ዋጋ ከተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ተ.ዕ.ታ) በፊት በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዥ ላይ በዝርዝር በማመልከት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ አዲስ አበባ ሳሪስ አቦ ከፋፋ የምግብ አክሲዮን ማህበር ጀርባ ወይም EBG /VOLVO ቀጥሎ ወደ ዉስጥ በሚያስገባው መንገድ 100 ሜትር ገባ ብሎ ስልክ ቁጥር፡- 0920577343 ፣ 0911166473 ፣ 0949632090

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን

✨ messages.ai_summary
The Ethiopian Agricultural Businesses Corporation is selling used light vehicles, heavy vehicles, trailers, buses, farm machinery and dozers in three lots via open bid. Bidders must buy the tender document, submit a CPO bid bond per lot, and quote prices excluding VAT.
Save Tender