Tender Detail

Tender Details

  • Company የወላይታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
  • Address ወላይታ ሶዶ ፡ ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 046 551 2116
  • Website
  • Deadline23 Oct 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceየማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ለእያንዳንዱ ሠነድ
  • Bid Securityለእያንዳንዱ ሎት ብር 60,000
  • opening dateበዕለቱ 8፡30 በመምሪያው የጨረታ አዳራሽ
  • Categories Printing And Publishing , Vehicle (Garage Service) , Vehicle Spare Parts

የመኪና ጥገና፣ የመኪና መለዋወጫ፣ የሞተር ጥገናና መለዋወጫ እና የማጣቀሻ መጻሕፍት ሕትመት ግዥ (ወዞፋ/ግ/02/2019) - የወላይታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ

የወላይታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ወዞፋ/ግ/02/2019

የወላይታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት በዞን ማዕከል ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች ከዚህ በታች በሎት የተጠቀሱ አገልግሎቶች እና ዕቃዎች ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች ለመፈጸም ይፈልጋል።

ሎትየሚገዛው ዕቃየጨረታ ማስከበሪያ
1የመኪና ጥገና አገልግሎት ግዥ60,000
2የመኪና መለዋወጫ ዕቃ ግዥ60,000
3የሞተር ጥገናና መለዋወጫ ዕቃ አገልግሎት ግዥ60,000
4የማጣቀሻ መጻሕፍት ሕትመት ግዥ60,000

ስለዚህ ተጫራቾች፡-

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ሰርተፊኬት፣ የታክስ ከፋይነት ማረጋገጫ (ቲን) ሰርተፊኬት እና የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ወይም (e-GP) ማቅረብ አለባቸው፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ የያዘ ሠነድ ለመግዛት ሲመጡ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ኮፒ እና የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ለእያንዳንዱ ሠነድ እየከፈሉ ከወላይታ ዞን ፋይ/ፕ/ል/ መምሪያ 2ኛ ፎቅ ከቢሮ ቁጥር 3 ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የአንዱን ዕቃ ወይም አገልግሎት ግዥ ዋጋ የሚያቀርቡበትን የመወዳደሪያ ሀሳባቸውን በጨረታ ሰነድ ላይ በተዘጋጀው ዋጋ መሙያ በመሙላት በታሸገ ፖስታ በወላይታ ዞን ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን በጨረታ አዳራሽ ቢሮ ቁጥር 19 መከተት ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያውን ሰነድ 1 ኦሪጅናል እና 1 የኦርጅናሉን ፎቶ ኮፒ ለብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ ሙሉ አድራሻቸውን በመጥቀስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ መከተት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዕለቱ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመምሪያው የጨረታ አዳራሽ ይከፈታል። 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
  6. አሸናፊ ድርጅት አስፈላጊውን ውለታ በመፈጸም ዕቃውን ሙሉ በሙሉ ወላይታ ዞን ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ ድረስ በማቅረብ ገቢ ሲያደርግ ክፍያ የሚፈጸም ይሆናል፡፡
  7. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0465512116 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የወላይታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ

✨ messages.ai_summary
Wolayita Zone Finance Department seeks suppliers for vehicle repair services, vehicle spare parts, motor repair and spare parts, and printing of reference books, in four lots. Bidders need a renewed trade license, VAT certificate, TIN certificate, and supplier registration or e-GP.
Save Tender