በአብክመ ሰሜን ሸዋ ዞን የአጣዬ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በስሩ ላሉ ሴክተር ጽ/ቤቶች የጽህፈት መሳሪያዎች፣ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ የጽዳት እቃ እና ደንብ ልብስ ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በሰሜን ሸዋ ዞን የአጣዬ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2019
በአብክመ ሰሜን ሸዋ ዞን የአጣዬ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በስሩ ላሉ ሴክተር ጽ/ቤቶች የጽህፈት መሳሪያዎች፣ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ የጽዳት እቃ እና ደንብ ልብስ ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::
ስለሆነም
- በዘርፉ የወጣ ንግድ ፈቃድና በዘመኑ የታደሰ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የምትችሉ
- መለያ ቁጥር /ቲን/ ፣ ግዥው ከ500,000/አምስት መቶ ሺህ /ብር በላይ መሆኑ ሲታመን ተጫራቹ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ በማድረግ ማቅረብ የምትችሉ
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-2 የተዘረዘሩትን ማስረጃዎችን በግልጽ የሚታይ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው
- የሚገዙ ዕቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ/ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ::
- ተጫራቾች በቀረበው ዝርዝር መስረት ለሚጫረቱበት ጠቅላላ ዋጋ 25000/ሃያ አምስት ሺህ ብር ብቻ/ የጨረታ ማስከበሪያ የግዥ መመሪያው በሚፈቅደው ማሲያዣ መሰረት በCPO ወይም በጥሬ ገንዘብ በአጣ/ከ/አስ/ ገንዘብ ጽ/ቤት ገቢ በማድረግ / ደረሰኙን ማቅረብ ይኖርባችኋል::
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 400/አራት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ከአጣ/ከ/አስ/ ገንዘብ ጽ/ቤት መግዛት ትችላላችሁ::
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ለ10 ተከታታይ ቀናት ከጠዋ 2:30 እስከ 11:30 ሰዓት ከአጣ/ከ/አስ/ ገንዘብ ጽ/ቤት ዘወትር በስራ ሰዓት በመቅረብ መግዛትና ለዚሁ በተዘጋጀው በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ትችላላችሁ::
- ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ታሽጎ በዚሁ ዕለት በ4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል:: ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል::
- ጨረታው በ11ኛው ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል::
- ተጫራቾች በራሳቸው የዋጋ ማቅረቢያ ሞልተው ማቅረብ አይችሉም::
- ተጫራቾች የጨረታውን ዋጋ ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ መሆን የለበትም፤ ከሆነ ከውድድር ውጭ ይሆናል::
- መ/ቤቱ ግዥውን ውል ከመፈፀሙ በፊት የቀረበውን ዋጋ ሳይቀይር እስከ በ20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል::
- በጨረታ አሸናፊው ተጫራች ለጽ/ቤቱ ባቀረበው የዋጋ ዝርዝር ከጠቅላላ ዋጋ ከነቫቱ 10% የውል ማስከበሪያ በCPO ወይም በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ውል የመፈረም ግዴታ ያለበት መሆኑን ማወቅ አለበት::
- በጨረታ አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈበትን እቃ ሙሉ በሙሉ በጽ/ቤቱ ንብረት ክፍል ባለበት ቦታ ማስረከብ እንዳለበት ማወቅ ይኖርበታል::
- ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ተጫራቾች የተናጠል ዋጋ ሲሞሉ ወደ ጎን ድምር በመደመር መሙላታቸሁን መዘንጋት የለባችሁም::
- ጨረታው በአብክመ የመንግስት ግዥ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 144/2018 መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል::
ማሳሰቢያ :-
- መረጃ መጠየቅ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0336610688 ወይም 0910663422 ላይ በመደወል መጠየቅ ይቻላል::
- ጨረታውን የምናወዳድረው በሎት ስለሆነ በሎቱ ውስጥ ላሉ ዕቃዎች በሙሉ ዋጋ መሞላት አለበት፤ ተጫራቹ ካልሞላ ከውድድር ውጭ ይሆናል::
- የገዙትን የጨረታ ሰነድ ምንም ሳያስቀሩ የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ሳይቀናነስ መመለስ ይኖርባችኋል::
- በዚሁ ጽ/ቤት ቀደም ሲል ለውድድር ተጋብዘው አሸናፊ ሆነው ለማቅረብ ፈቃደኛ ያልሆኑ ነጋዴዎችን በሙሉ የማናሳትፍ መሆኑን ማወቅ ይኖርባችኋል::
የሰሜን ሸዋ ዞን የአጣዬ ከተማ አስተደደር ገንዘብ ጽ/ቤት
አጣዬ
✨ messages.ai_summary
Ataye Town Administration Finance Office seeks suppliers for stationery, consumable office supplies, cleaning materials, and uniforms for its sector offices via open tender. Bidders need a valid trade license, renewed photo copy, TIN, and VAT registration proof. Items must be priced per lot.
