Tender Detail

Tender Details

  • Company Modjo Customs Branch Office (የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት)
  • Address ሞጆ ፡ ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0222369094
  • Website
  • Deadline13 Oct 2026, 11:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityየሚጫረትበትን ጠቅላላ ዋጋ 5% (CPO)
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure , Cloth And Shoes

የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተወረሱና በተተዉ እቃዎች አወጋገድ መመሪያ መሰረት የተለያዩ እቃዎችን፣ አልባሳት፣ ጫማዎች፣ ቦርሳዎች፣ ሽቶዎች፣ የብረት ቁሳቁሶች፣ የተለያዩ መለዋወጫዎች እና ECOLOGIC COFFEE WET MILL ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

Modjo Customs Branch Office (የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት)


የተተውና የተወረሱ ዕቃዎች ግልፅ ጨረታ

ቁጥር ግ09/2019 ዓ.ም

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስመጪዎች በተሻሻለው የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 1160/2011 መሰረት የተተው ወይም የተወረሱ ዕቃዎችን በእቃ አወጋገድ መመሪያ ቁጥር 167/2012 አንቀጽ 9 መሠረት የተተውና የተወረሱ ንብረቶችን ማለትም SCHOOL & TRAVELLING BAGS፣ አልባሳት፣ ጫማዎች፤ ሽቶዎች፤ ፔርሙዝ እና ሌሎች እቃዎች፣ SPRING LOCK, HNGES SET COMPLETE, ALUMINIUM SCRAP & TOP WINDOW HOLDING ARMS WITH COMPLETE SCREWS፤ POLYESTER FUR JACKET እና ECOLOGIC COFFEE WET MILL እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በዚህም መሠረት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን : ጀምሮ : ለመጫረት የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን::

  1. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር፣ ዓይነት፣ ብዛት፤ የጨረታ ሠነድ እና መመሪያ ከአክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በመግባት ከንብረቶቹ መግለጫ ስር ተያይዞ የሚገኝ ሲሆን አውርደው መመልከት ይኖርባቸዋል:: ተጫራቾች ከአክሽን ኢትዮጵያ ላይ ተመዝግበው የጨረታ ሰነዱን ካገኙ በኋላ ንብረቶችን በአካል ለመመልከት ዘወትር ከሰኞ እስከ ሐሙስ ከጠዋት 2:00 እስከ ቀኑ 6:00 ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7:00 እስከ ቀኑ 10:30 እና ዓርብ ከጠዋት 2:00 እስከ ቀኑ 5:00 ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7:30 እስከ ቀኑ 10:30 እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋት 2:00 እስከ ቀኑ 5:30 መመልከት ይችላሉ::
  2. የጨረታ ሰነዱን ከአክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም /ድረገፅ/ ኦንላይን ላይ ብቻ መግዛት እና መጫረት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን::
  3. ተጫራቾች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር በዘርፉ የፀና ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ በአክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ማያያዝ አለባቸው:: ሆኖም ግምታዊ ዋጋቸው ከብር 500,000.00 በታች የሆኑ ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሠርተፍኬት ማቅረብ ሳያስፈልግ መወዳደር ይችላሉ::
  4. ማንኛውም ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን የሚጫረትበትን ጠቅላላ ዋጋ 5% ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ጨረታ ከመከፈቱ በፊት በ ETHIOPIAN CUSTOMS COMMSSON MODJOBRANCH OFFICE በሚል ሥም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከአዲስ አበባ፣ አዳማ እና ሞጆ ቅርንጫፎች ብቻ አሰርተዉ አክሽን ኢትዮጵያ ሂደዉ በማስያዝ ወይም በአክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ ባለው የሲፒኦ አማራጮች ኦንላይን ማስያዝ ይኖርባቸዋል::
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በመግዛት የሚወዳደሩበትን ዕቃ አስቀድሞ ማየት ያለባቸው ሲሆን ዕቃውን ሳያዩ ለሚሞሉት ዋጋ ቅ/ጽ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም:: በጨረታ ተሸጦ የተወሰደ እቃ ተመላሽ አይደረግም፤ ለእቃውም የተከፈለ ገንዘብ አይመለስም::
  6. ተጫራቾች የአክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethiopia] ብለው በማውረድ ወይም (auction.et) ላይ መመዝገብ እና መጫረት ይችላሉ::
  7. የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 8ኛው የሥራ ቀን ጠዋት 5:00 ድረስ በኦክሽን ኢትዮጵያ ኦንላይን ፕላትፎርም መወዳደሪያ ዋጋ ማስገባት ይችላሉ:: ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የጨረታውን ሂደትና ውጤት ኦንላይን መከታተል ይችላሉ::
  8. ተጫራቾች የሚያስገቡት ዋጋ 15% ቫትን ያካተተ መሆን አለበት::
  9. ማንኛውም በግልጽ ጨረታ የሚሳተፍ ተጫራች ጨረታው ከተጀመረ በኋላ ዋጋ መቀየር ወይንም የሌላ ተጫራቾችን ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ አሻሽሎ ማቅረብ አይችልም፤ በጨረታ ሽያጭ ውድድር ላይ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤት እና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም፣ ጨረታው ተጀምሮ ዋጋ ከሰጡ በኋላ እራሱን ከጨረታ ውድድር ማግለል አይቻልም እና የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ግምገማ ተጠናቆ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የጨረታውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል::
  10. የግልጽ ጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ስለማሸነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ የአሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ አለበት:: በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ ገንዘቡ ገቢ ካልተደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል።
  11. በተራ ቁጥር 10 በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ የአሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ አድርጎ ዕቃውን ያላነሳ/ ያልተረከበ እንደሆን ለሚቆይበት ለተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ ይከፍላል:: ሆኖም ዕቃው በ2 (ሁለት) ወራት ውስጥ ካልወጣ እንደተተወ ተቆጥሮ በጨረታ ሽያጭ ይወገዳል።
  12. አሸናፊው ተጫራች ዕቃዎችን ለመረከብና ለማጓጓዝ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን ሁሉ ራሱ ይሸፍናል::
  13. ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ለጨረታ የአቀረበውን ዕቃ ብዛት ለመጨመርም ሆነ ለመቀነስ ሙሉ መብት አለው:: በጨረታ ተሸጦ በጨረታ አሸናፊው የተወሰደ እቃ አይመለስም::
  14. የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በአጭር ስልክ ቁጥር መስመር 9164 ወይም 09-05-11-55-11/011-666-8828 በመደወል ማግኘት ይቻላል::
  15. ለተጨማሪ ማብራሪያ በሥልክ ቁጥር 022-236-90-94 /022-236-01-90 ላይ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ::

በጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Ethiopian Customs Commission's Modjo branch invites bids to sell abandoned and seized goods, including bags, clothes, shoes, perfumes, metal items, spare parts, and an ECOLOGIC COFFEE WET MILL. Bidders need a valid trade license, TIN, and tax compliance; VAT registration is waived for lots under 500,000 birr.
Not stated in the notice: opening date, bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender