Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Capital Market Authority (ECMA) (የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን)
  • Address ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ምናዬ ኮርፖሬት ቢሮ ፓርክ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-5-57-83-27
  • Websitehttps://ecma.gov.et/
  • Deadline19 Oct 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን እና ሪፖርተር
  • Bid Document Price300.00
  • Bid Securityብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ዋስትና ወይም ሲፒኦ
  • opening dateጥቅምት 9 ቀን 2019 ከሰዓት በ4:30
  • Categories Rent , Land, House, Building And Warehouse Rent

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን የቢሮ ቦታ ኪራይ ግዥ (Procurement of Rental of Secure Office Space) በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አገልግሎቱን ለመግዛት ይፈልጋል

Ethiopian Capital Market Authority (ECMA) (የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን)


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡- ECMA/NCB/OB/02/2019

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ባለው በጀት የቢሮ ቦታ ኪራይ ግዥ (Procurement of Rental of Secure Office Space) ግዥ በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አገልግሎቱን ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሰረት፡-

  1. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን እና ሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መከፈቻ ቀን ድረስ የማይመለስ 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመ/ቤታችን አካውንት 1000586364824 ገቢ በማድረግ ከባለሥልጣኑ ፋይናንስና ግዥ ክፍል የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የመወዳደርያ ሰነዳቸውን ፋይናንስና ቴክኒካል ኦሪጅናልና ኮፒ ለየብቻ በማሸግ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ጨረታው መዝጊያ ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች በዘርፉ ያላቸውን በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የግብር ክሊራንስ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፤ በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድረ-ገጽ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ማስረጃቸውን እንዲሁም የተፈረመና ማህተም ያለው የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈፀም ቃል የተገባበት ቅጽ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች ዋጋቸውን በመሙላት ባለሥልጣኑ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከጨረታ መዝጊያ ሰዓት በፊት ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርቡና ስርዝ ድልዝ ያለው የጨረታ መወዳደሪያ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
  5. ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ለ15 ቀናት ብቻ ነው፡፡
  6. ተጫራቾች በሚያቀርቧቸው ሰነዶች ላይ የድርጅታቸውን ማህተምና የተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪል ፊርማ መኖር ይገባዋል፡፡
  7. አሸናፊው ተጫራች አገልግሎቱ በተፈለገ ጊዜ አገልግሎቱን የመስጠት ሃላፊነት አለበት፡፡
  8. ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበርያነት የብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ዋስትና ወይም ሲፒኦ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  9. ተጫራቾች የቀረበውን ዝርዝር መስፈርት መሰረት በማድረግ የሚያቀርቡትን አገልግሎት ዝርዝር የቴክኒክ መግለጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  10. አንዱ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  11. ጨረታው ጥቅምት 9 ቀን 2019 ከሰዓት በ4:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከሰዓት በ4:30 ላይ ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በባለስልጣኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  12. በጨረታው መከፈቻ ዕለት የተጫራቾች አለመኖር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉለውም፡፡
  13. ባለሥልጣኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. ተጨማሪ ማብራርያ ካስፈለገ በአካል የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን አድራሻ ቦሌ መንገድ ፍላሚንጎ ሪስቶራንት ገባ ብሎ ባለው ዋ/መ/ቤት በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን
የፋይናንስና ግዥ ዳይሬክቶሬት
ከፍላሚንጎ ሪስቶራንት ወደ አደራ ሆስፒታል በሚወስደው መንገድ ምናዬ ህንፃ
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
ስልክ 011-5-57-83-27
ኢሜል: Procurement@ecma.gov.et

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን

✨ messages.ai_summary
Ethiopian Capital Market Authority seeks to procure rental of secure office space via national competitive bidding. Bidders must submit financial and technical proposals separately, with renewed business license, registration, VAT and tax clearance certificates, and proof of registration on the government procurement portal.
Save Tender