Tender Detail

Tender Details

  • Company Tsedey Bank S.C. (ፀደይ ባንክ አ.ማ)
  • Address ሰንጋተራ አካባቢ በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት ህንጻ 16ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 09 ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0115584896
  • Websitehttps://tsedeybank-sc.com/
  • Deadline20 Oct 2026, 10:00 AM
  • magazineREPORTOR
  • Bid Document Price500(አምስት መቶ ብር)
  • Bid Securityየአጠቃላይ ዋጋውን 2% ወይም ከብር 500,000.00 የሚበልጥ ከሆነ ብር 500,000.00 (CPO ወይም ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ፣ ለ90 ቀን)
  • opening dateጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30
  • Categories Furniture And Furnishing , Finishing Work , Interior Design Service And Material

ፀደይ ባንክ አ.ማ የካውንተር ስራ ለአንድ አመት ቋሚ ውል በመያዝ ለማሰራት ግዥ ለመፈፀም ፈቃድ ያላቸውን ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል::

Tsedey Bank S.C. (ፀደይ ባንክ አ.ማ)


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ብ/ግ/ጨ/004/2019

ፀደይ ባንክ አ.ማ የካውንተር ስራ ለአንድ አመት ቋሚ ውል በመያዝ ለማሰራት ግዥ ለመፈፀም ፈቃድ ያላቸውን ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል:: ስለሆነም ከዚህ በታች የተቀመጠውን መስፈርት የሚያሟላ ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ ድርጅት/ካጋዶ/ መወዳደር የሚችል መሆኑን እንገልጻለን::

  1. የ2018 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት፣ የግብር መክፈያ ሰርቲፊኬት፣ የታክስ ክሊራንስና የብቃት ማረጋገጫ ሲኖራቸዉ ይገባል:: ቴክኒካል ዶክሜንትና የሚያቀርቡበትን ዋጋ በጨረታ ዶክሜንቱ መሰረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
  2. ለጨረታ ማስከበሪያ የአጠቃላይ ዋጋውን 2% ወይም የአጠቃላይ ዋጋው 2% ከብር 500,000.00 የሚበልጥ ከሆነ ብር 500,000.00 በሲፒኦ /CPO/ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ለ90 ቀን በፀደይ ባንክ አ.ማ ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል:: ከየትኛውም የፀደይ ባንክ አ.ማ ቅርንጫፍ የተሰጠ ሲፒኦም ሆነ ባንክ ጋራንቲ ተቀባይነት የለውም ::
  3. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከመስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት የስራ ቀናት ማለትም ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት እና ከሰዓት በኋላ ከ7:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 11:00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት የማይመለስ አምስት መቶ ብር /500.00/ ፀደይ ባንክ ለገሀር ቅርንጫፍ ወይም በማንኛውም የፀደይ ባንክ ቅርንጫፍ በመክፈል ስንጋተራ አካባቢ በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት 16ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 09 ከግዥ ክፍል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ::
  4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ በሰም በታሸገ ፖስታ እስከ ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ አዲስ አበባ ስንጋተራ አካባቢ በሚገኘው ፀደይ ባንክ ዋና መ/ቤት 16ተኛ ፎቅ ግዥና ዉል አስተዳደር ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል:: ጨረታው በዚሁ ዕለት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ 4:30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመስሪያ ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል::
  5. የጨረታዉ መዝጊያ ሰዓት ካለፈ በኋላ የሚመጣ ማንኛዉም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረዉም::
  6. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

አድራሻ ፡- አዲስ አበባ ስንጋተራ አካባቢ ጤና ሚኒስቴር ዝቅ ብሎ በሚገኘው የፀደይ ባንክ ዋና መ/ቤት ስልክ ቁጥር 011 5581658

ፀደይ ባንክ አ.ማ

✨ messages.ai_summary
Tsedey Bank S.C. seeks eligible bidders to provide counter work under a one-year fixed contract. Bidders must hold a renewed business license, VAT certificate, tax payment certificate, tax clearance, and competency certificate, and submit technical and financial documents.
Save Tender