የቢሮ ዕቃዎች የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ።
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት የኢትዮጵያ ስነመለኮት ድህረምረቃት/ቤት እና የፍ/ባለዕዳ ኤንቢ.ጂ ኮንስትራክሽን ትሬዲንግ ህ/የተ/የግ/ማህበር መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/325853 በ03/02/2018ዓ/ም እና በመ/ቁጥር 328966 በ26/09/2018ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 04 የኢትዮጵያ ስነ መለኮት ህንጻ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ የቢሮ ዕቃቃዎች የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 146,609 20 ( አንድ መቶ አርባ ስድስት ሺህ ስድስት መቶ ዘጠኝ ከ20/100) ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 4:00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡
የሐራጅ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3:30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጎብኘት የሚችሉ ሲሆን፣እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም C.P.O አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን ፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጥ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
