Tender Detail

Tender Details


የቡራዩ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለስልጠና የሚያስፈልጉትን የግብርና ስራ፣ የኮንስትራክሽን፣ የICT፣ የኤሌክትሪክ፣ የቧንቧ፣ አውቶሞቲቭ፣ የደንብ ልብስ፣ የፈርኒቸር፣ የኢንዱስትሪያል ኤሌክትሪሲቲ፣ GMFA እና Hair dressing ስልጠና የሚውሉ እቃዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

የቡራዩ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ


የጨረታ ማስታወቂያ

የቡራዩ ፖሊ/ቴክኒክ ኮሌጅ ለስልጠና የሚያስፈልጉትን የግብርና ስራ ፤ የኮንስትራክሽን ፤ የICT ፤ የኤሌክትሪክ፤ የቧንቧ፤ አውቶሞቲቭ ፤ የደንብ ልብስ ፤ የፈርኒቸር ፤ የኢንዱስትሪያል ኤሌክትሪክ ሲቲ፤ GMFA፤ ለ Hair dressing ስልጠና የሚውሉ እቃዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ዝርዝር ሁኔታዎች

ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከቡራዩ ፖሊ. ቴክኒክ ኮሌጅ የማይመለስ ብር. 2000.00( ሁለት ሺህ ብር) በመክፈል ስለዕቃዎቹ የሚገልፅ ሰነድ (ዶክመንት) ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን- ከቡራዩ ፖሊ. ቴክኒክ ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር 11 ዘውትር በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡

  1. በዕቃ ዓይነት የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ በስማቸው ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ግዥው(አገልግሎቱ) ከ100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ) ብር በላይ ከሆነ የቫት (የተጨማሪ እሴት ታክስ) ተመዝጋቢና የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለዉ፡፡ እንዲሁም በፌዴራል ገ/ኢ/ ልማት ሚኒስቴር ወይም በኦሮሚያ ገ/ኢ/ል/ቢሮ ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር ) በባንክ የተመሰከረ ወይም CPO (ሲፒኦ) የጨረታ ዋስትና ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛቀን ከቀኑ-4:00- ቢሮ ቁጥር 06 ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
  5. ጨረታው 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን 4:30 ላይ ይሆናል በዚሁ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  6. ኮሌጁ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥሮች (0913154549) መደወል ይችላሉ

የቡራዩ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

✨ messages.ai_summary
Burau Polytechnic College seeks to purchase training equipment and materials for agriculture, construction, ICT, electrical, plumbing, automotive, garment, furniture, industrial electricity, GMFA, and hairdressing training. Bidders must hold a renewed business license for the item type, be tax-compliant, and if the purchase exceeds 100,000 birr, be VAT-registered and listed as a supplier.
Save Tender