የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90፣ 216/92 እና 1147/2011 መሰረት በብድር ዕዳ ምክንያት የተረከባቸውን ከዚህ በታች በሰንጠረዥ የተዘረዘሩትን ንብረቶች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
Development Bank of Ethiopia (የኢትዮጵያ ልማት ባንክ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90፣ 216/92 እና 1147/2011 መሰረት በብድር ዕዳ ምክንያት የተረከባቸውን ከዚህ በታች በሰንጠረዥ የተዘረዘሩትን ንብረቶች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
| ተ.ቁ | የተበዳሪው/ የመያዣ ሰጪው ስም | የንብረት/ፕሮጀክት አድራሻ | የንብረት/ፕሮጀክት ዝርዝር | የቦታ ስፋት | የጨረታ መነሻ ዋጋ (በብር) | የጨረታ ሁኔታ | የጨረታ ደረጃ | ጨረታው የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት |
| 1. | አቶ ግርማ አፈወርቅ መድምም | በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንፋስ ስ/ላ/ክ/ ከተማ ወረዳ 08 | ጋቴፓሮ ቆርቆሮ ፋብሪካ፣የህንፃ ግንባታዎች፣ የኤሌክትሪክ ሥራዎች፣ ማሽነሪዎች፣ ቁሳቁሶች፣ የቢሮ ዕቃዎችና መገልገያዎች፣ የጥሬ ዕቃና የምርት ክምችት | 1,678 ካ.ሬ ሜትር | 137,956,256.00 (አንድ መቶ ሰላሳ ሰባት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሃምሳ ስድስት ሺህ ሁለት መቶ ሃምሳ ስድስት ብር) | ዝግ | አንደኛ | ጥቅምት 30 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00-6፡00 ሰዓት |
ማሳሰቢያ፤
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በመግዛት ንብረቶቹን የሚገዙበትን ዋጋ፣ ስምና አድራሻቸውን በፎርሙ ላይ በመሙላት በባንኩ ዋና መ/ቤት ሁለተኛ ታወር ምድር ቤት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣ ከሦስተኛው ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅም 26 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡50 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 10 በመቶ በባንክ ክፍያ ማዘዣ /ሲ.ፒ.ኦ/ ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡
- አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 /በአስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሰንጠረዥ በተመለከቱት ቀናት 4፡00 ሰዓት ላይ ተከፍቶ እስከ 6፡00 ሰዓት በባንኩ ዋናው መ/ቤት ይካሄዳል፡፡ ህጋዊ ሰውነት ያላቸው አካላትን ወክሎ በጨረታው ለመሳተፍ የሚቀርብ ሰው የማህበሩ መመስረቻ ጽሁፍ/መተዳደሪያ ደንብ ከእነ ማሻሻያዎቹ (ካለ)፣ የንግድ ምዝገባ፣ የንግድ ፍቃድ፣ ሌሎች አስፈላጊ ማስረጃዎችን እና የተረጋገጠ የውክልና ስልጣን ሰነዶችን ይዞ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
- 15% የተጨማሪ እሴት ታክስና ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎችን፣ የስም ማዛወሪያ ክፍያን ጨምሮ ገዢው ይከፍላል፡፡
- አንዳንድ የድርጅቶቹ ንብረቶች የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ያልተከፈለባቸው ስለሆኑ ገዢው የቀረጥ ነፃ መብት ሊኖረው አሊያም የሚፈለገውን ቀረጥ/ታክስ ለመንግስት ለመክፈል ይገደዳል፡፡
- የንብረት ሽያጩ ሙሉ በሙሉ በጥሬ ገንዘብ ብቻ ይሆናል፡፡
- የንብረቱ ስመ-ንብረት ለገዥው እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይፅፋል፡፡ ገዥው ጉዳዩን ተከታትሎ ያስፈፅማል፡፡
- ተጫራቾች ንብረቱን ለመጎብኘት ከፈለጉ አስቀድሞ ከባንኩ ጋር ቀጠሮ በመያዝ ንብረቱን መጎብኘት ይችላሉ፡፡
- በጨረታ ሂደቱ ላይ መሳተፍ የሚችሉት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ይሆናሉ፡፡
- በጨረታው ዝርዝር እና ተጨማሪ መረጃን ለማግኘት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዋና መ/ቤት ታወር ሁለት ሦስተኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የአንጎይንግ ኮንሰርን ፕሮጀክትስ እና አኳየርድ አሴትስ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011-524-53-73/ 011-524-42-69 ደውሎ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
✨ messages.ai_summary
The Development Bank of Ethiopia invites bids to purchase foreclosed assets, including a Gatteparo corrugated iron factory with buildings, electrical works, machinery, materials, office items, and raw material and product stock. Bidders must pay 15% VAT and other legally required fees, including transfer fees.
