Tender Detail

Tender Details

  • Company የመሀል ግንፍሌ የመጀ/ደ/ት/ቤት
  • Address አራት ኪሎ አለ የስነጥበብና ዲዛይን ት/ቤት ወደም አዲስ የእናቶችና ህፃናት ሆስፒታል አጠገብ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 1 54 45 31
  • Website
  • Deadline14 Oct 2026, 10:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price200
  • Bid Securityብር 5000.00 /አምስት ሺህ ብር/ CPO (ሲፒኦ)
  • opening dateበ11ኛው ቀን በ4:30 ሰዓት ላይ ይከፈታል
  • Categories Office And Home Furniture , Stationery Materials , Cloth And Shoes

የመሀል ግንፍሌ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የደንብ ልብስ፣ ጫማ፣ አላቂ የቢሮና የትምህርት እቃዎች፣ ከለር ፕሪንተር፣ ቴሌቪዥን፣ ጠረጴዛዎች፣ ወንበሮች እና ሌሎች ተዛማጅ እቃዎችን መግዛት እና የሠራተኞች የደንብ ልብስ ስፌት ማሰፋት ይፈልጋል

የመሀል ግንፍሌ የመጀ/ደ/ት/ቤት


የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 01/2019 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአራዳ ክ/ከተማ የመሀል ግንፍሌ የመጀ/ደ/ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም በጀት አመት ነጭ የጋውን የደንብ ልብስ ፖሊስተር 6000፣ የደንብ ልብስ ካኪ ፖሊስተር 6000፣ በቢለን ጨርቅ፣ ቆዳ ጫማ የወንድና የሴት፣ የስፖርት ቱታ እና ሸራ ጫማ የሴት፣ ቱታ የአትክልተኛ፣ ሸሚዝ እጀ ሙሉ፣ የፕላስቲክ ቡቲ ጫማ፣ የሱፍ ካፖርት፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ አላቂ የትምህርት እቃዎች፣ ሌሎች አላቂ እቃዎችና አቅርቦቶች፣ ከለር ፕሪንተር፣ ቴሌቪዥን፣ ሞንታርቦ፣ እስካነር፣ ፍሪጅ፣ ሬዲዮ፣ የተለያዩ ጠረጴዛዎች፣ የተለያዩ ወንበሮች፣ ፋይል ካቢኔት ባለብረት፣ ኤል ሼፕ ሶፋ፣ ጥቁር ሰሌዳ እና ሌሎች ተዛማጅ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና የሠራተኞች የደንብ ልብስ ስፌት ማሰፋት ይፈልጋል።

ተጫራቾች የሚከተሉትን ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላት ይገባቸዋል።

  1. በተሰማሩበት የሥራ መስክ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN NO/ ያላቸው፣ ሕጋዊ ደረሰኝ ያላቸው፣ በአቅራቢ ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን ይኖርባቸዋል።
  2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባዘጋጀው የእቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተመሰከረለት CPO (ሲፒኦ) ብር 5000.00/አምስት ሺህ ብር/ በመስሪያ ቤቱ ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በማየት ናሙና የሚቀርብባቸውን እቃዎች ናሙና ማቅረብ ናሙና የማይቀርብባቸውን እቃዎች በከለር ፎቶ የተደገፈ ማስረጃ ከናሙናው ጋር ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  5. ጨረታውን የሚያሸንፈው ድርጅት እቃዎቹን እስከ ት/ቤቱ ማድረስ አለበት።
  6. ጨረታው አየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ11 (አስራ አንድ) ተከታታይ የሥራ ቀናት ይሆንና በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ታሽጎ በ4:30 ሰዓት ላይ ይከፈታል። የጨረታውን ሰነድ ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒ ቫትን ጨምሮ ተሟልቶ ለየብቻው በፖስታ ታሽጎ ሲፒኦ በኦርጅናል ውስጥ በማድረግ ቢሮ ቁጥር 3 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል። የተገዛው የጨረታ ሰነድ ሙሉ በሙሉ በተጫራቾች ዋጋው ተሞልቶ በየገፁ ተፈርሞበት መግባት አለበት።
  7. በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ተቋማት ራሳቸው አምርተው ለገበያ በሚያቀርቡት ዕቃ ወይም እሴት ጨምረው ለሚያመርቱት ምርት ካልሆነ በስተቀር የተዘጋጁ እቃዎችን ገዝተው ለሚወዳደሩበት እንደማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ መግዛትና የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
  8. ተጫራቾች ስርዝ ድልዝ፣ የማይነበብ ሰነድ፣ የዘገየ ሰነድ፣ ጨረታ ላይ ያልተነበበ የዋጋ ማቅረቢያ፣ ከገዙት ጨረታ ሰነድ ውጭ ተሞልቶ የሚመጣ ሰነድ እና ቀነ ገደብ የሚያስቀምጥ ተቀባይነት አይኖረውም።
  9. አሸናፊ ተጫራች 10% የውል ማስከበሪያ CPO (ሲፒኦ) በመስሪያ ቤቱ ስም ማስያዝ አለባቸው።
  10. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘውን ሰነድ የማይመለስ 200 ብር /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
  11. መሥሪያ ቤቱ ለግዢው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- አራት ኪሎ አለ የስነጥበብና ዲዛይን ት/ቤት ወይም አዲስ የእናቶችና ህፃናት ሆስፒታል አጠገብ

ስልክ ቁጥር፡- 011 1 23 28 40 / 011 1 54 45 31 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

የመሀል ግንፍሌ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት

✨ messages.ai_summary
Mehal Ginfile Primary School seeks to buy staff uniforms, shoes, stationery, office and educational materials, a color printer, TV, tables, chairs and related items, plus tailoring of staff uniforms. Bidders need a renewed trade license, TIN, VAT registration, supplier-list certificate, and samples or photos.
Save Tender