Tender Detail

Tender Details

  • Company በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጉምሩክ ኮሚሽን የጋላፊ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
  • Address ሰመራ ፡ አፋር ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0335590114
  • Website
  • Deadline08 Oct 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100(አንድ መቶ ብር)
  • Bid Securityበምድብ: ምድብ 4፣5፣6 ብር 50,000 እያንዳንዳቸው፤ ምድብ 11 ብር 300,000 (CPO)
  • opening dateበ28/01/2019ዓ.ም ከጠዋት 4:00 ሰዓት ይከፈታል
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure , Disposal Sale

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጉምሩክ ኮሚሽን የጋላፊ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ የንጽህና መጠበቂያ ዘርፍ እቃዎች እና ልዩ ልዩ ዘርፍ እቃዎች በሀራጅ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 04/2019 ዓ.ም እቃዎቹን ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጉምሩክ ኮሚሽን የጋላፊ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 04/2019

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጉምሩክ ኮሚሽን የጋላፊ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ የንጽህና መጠበቂያ ዘርፍ እቃዎች እና ልዩ ልዩ ዘርፍ እቃዎች በሀራጅ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 04/2019 ዓ.ም እቃዎቹን ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡- ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

  1. በጨረታ ሽያጭ ስርዓት ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የጸና የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ ያለበት ሲሆን በሀራጅ ጨረታ ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች ከላይ የተጠየቁትን መረጃዎች በጨረታ መከፈቻ ቀን ይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡
  2. ከላይ በተራ ቁጥር አንድ የተገለጸው ቢኖርም ግምታዊ ዋጋው ከብር 500 ሺህ በታች የሆነ ማንኛውም እቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አያስፈልግም፡፡ እንዲሁም የሚሸጠው እቃ ተሽከርካሪ ሲሆን የተሽከርካሪው አስመጪ ወይም ባለቤቱ ቤተሰብ ከሆነ ሰው በስተቀር ማንኛውም እድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ ቅድመ-ሁኔታዎቹን ማሟላት ሳያስፈልገው በጨረታው ሊሳተፍ ይችላል፡፡
  3. በሀራጅ ጨረታ ለወጡት እቃዎች ለመሳተፍ ለምድብ 4 ልዩልዩ ዘርፍ እቃዎች ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር)፣ ለምድብ 5 ንጽህና መጠበቂያ ዘርፍ እቃዎች ብር 50,000(ሃምሳ ሽ ብር)፣ ለምድብ 6 ንጽህና መጠበቂያ ዘርፍ እቃዎች ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) እና ለምድብ 11 ልዩ ልዩ ዘርፍ እቃዎች ብር 300,000 (ሶስት መቶ ሺህ ብር) ለየብቻው የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ Cpo በቀጥታ አካውንት ቁጥር 1000296553216 በጋላፊ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስም በማሰራት የጨረታ ሰነዱን እና በተራ ቁጥር አንድ የተገለጹትን መረጃዎች በመያዝ በቀን 28/01/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ላይ መገኘት አለባቸው፡፡
  4. ከላይ በተራ ቁጥር 3 በተገለጸው መሰረት በቂ የጨረታ ማስከበሪያ ያላስያዘ ተጫራች መወዳደር ወይም መጫረት አይችልም፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2:00-6:00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከ9:00-12:00 የእቃዎቹን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100:00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ይህ ጨረታ በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 28/01/2019 ጠዋት 3:30 ድረስ በውርስ መጋዘን አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 08 መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. ለጨረታ የሚቀርቡ ዕቃዎች ለናሙና ዕይታ የሚቀርቡበት ጊዜ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት መስከረም 23/2019 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መስከረም 28/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:30 ድረስ ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት ከ2:00-6:30 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከ9:00-12:00 ሰዓት እና ቅዳሜ ጠዋት 2:00-6:00 ሰዓት የእቃዎቹን ዝርዝር መመልከት ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም ተጫራቾች የእቃውን ናሙና ሳያዩ በሰጡት ዋጋ ምክንያት ለሚፈጠር ቅሬታ በቅ/ጽ/ቤቱ ተጠያቂነት የለውም፡፡
  7. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ የጊዜ ሰሌዳ (ስኬጁል) መሠረት መጫረት ይችላሉ፡፡
ተ.ቁ የቅ/ጽ/ቤቱ ስም የጨረታው አይነት የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻ ቀንና ሰዓት
1 ጋላፊ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ሀራጅ ጨረታ እስከ 28/01/2019 ከጠዋቱ 3:30ድረስ በ28/01/2019ዓ.ም ከጠዋት 4:00 ሰዓት ይከፈታል

የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ

  1. የጨረታው መክፈቻ ቦታ፡- በጋላፊ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በቦታው ባይገኙም የጨረታ ሰነዱ በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች በተራ ቁጥር አንድ የተጠቀሱ ማስረጃዎች ኦርጅናል ይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡
  2. በተጫራቾች የተሰጠ የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ሂደት ተጠናቆ የጨረታው ውጤት እስከሚገለፅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል፡፡
  3. በጨረታ ለሚሸጥ እቃ የጨረታ ውጤት እንደተገለጸ ከአሸናፊው ጋር የሽያጭ ውል እንደተደረገ ይቆጠራል፡፡
  4. ምድብ ለወጣላቸው ሀራጅ እቃዎች ጨረታው የሚካሄደው በምድብ ሲሆን ተጫራቾች አሸናፊ የሚደረጉትም ለምድቡ ባቀረቡት የእያንዳንዱ እቃዎች ዋጋ ድምር ከፍተኛው ዋጋ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም ተጫራቾች በምድቡ ለቀረቡት ለእያንዳንዱ እቃዎች ዋጋ መስጠት አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች ከአሸነፉበት የእቃ ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ (15%) የሚጨመር ይሆናል፡፡
  6. ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) በተመለከተ ለአሸናፊው ተጫራች ካሸነፉት የዕቃ ዋጋ ላይ የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች የጨረታ ውጤቱ በተገለጸ በ3 (ሶስት) ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
  7. አሸናፊ ተጫራች ዕቃዎቹን ባሉበት ቦታ እና ሁኔታ የመረከብ ግዴታ አለበት፡፡ በተጨማሪም ለማጓጓዝ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን ሁሉ ራሱ ይችላል፡፡
  8. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ05 (በአምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን እቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ ያለበት ሲሆን ይህን ባይፈጽም ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት (CPO) ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ተደርጎ ዕቃው በድጋሚ ለጨረታ የሚቀርብ ሲሆን ነገር ግን አሸናፊው የአሸነፈበትን የእቃ ዋጋ ገቢ አድርጎ በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ እቃውን ያላነሳ እንደሆነ ለሚቆይበት ተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ የሚከፍል ይሆናል፡፡ ሆኖም እቃውን በሁለት ወር ውስጥ ካላወጣ በጨረታ የተከፈለው ዋጋ ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ሆኖ እቃው እንደተተወ ተቆጥሮ በሽያጭ ይወገዳል፡፡
  9. በጨረታ የሚሸጠው እቃ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ከመወረሱ በፊት የእቃው አስመጪ ወይም ባለቤትና በቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም፡፡
  10. ለጨረታ የቀረቡት እቃዎች የሚገኙበት ቦታ ጋላፊ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት መሆኑ ይታወቅ፡፡
  11. ኮሚሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ውርስ መጋዘን አስተዳደር የስራ ሂደት ስልክ ቁጥር 033-559-0114 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

በጉምሩክ ኮሚሽን የጋላፊ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
The Ethiopian Customs Commission's Galafi branch seeks to sell confiscated hygiene and miscellaneous goods via auction, as-is. Bidders need a valid business license, VAT registration, TIN, and tax payment proof. Vehicles may be bid on by any Ethiopian over 18, except the importer or owner's family.
Save Tender