የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ውሃና ፍሳሽ መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ዲቪዥን፡- ምድብ አንድ፡- የቶዮታ መኪና መለዋወጫ እቃዎች ምድብ ሁለት፡- የፎርድ መኪና መለዋወጫ እቃዎች ምድብ ሶስት፡- የጎማ እና ባትሪ እቃዎች ምድብ አራት፡- የመኪና ጌጣጌጥ እና ልዩ ልዩ እቃዎች ምድብ አምስት፡- ለተሽከርካሪ ጥገና የሚሆኑ የተለያዩ መፍቻዎች(Tools) በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ውሃና ሳኒቴሽን መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ዲቪዥን
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር AAWSA/WSIDD/GOV/NCB/G002/2019
የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ውሃና ፍሳሽ መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ዲቪዥን፡-
- ምድብ አንድ፡- የቶዮታ መኪና መለዋወጫ እቃዎች
- ምድብ ሁለት፡- የፎርድ መኪና መለዋወጫ እቃዎች
- ምድብ ሶስት፡- የጎማ እና ባትሪ እቃዎች
- ምድብ አራት፡- የመኪና ጌጣጌጥ እና ልዩ ልዩ እቃዎች
- ምድብ አምስት፡- ለተሽከርካሪ ጥገና የሚሆኑ የተለያዩ መፍቻዎች(Tools) በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎችን በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
- ተጫራቾች ዘወትር በስራ ሰዓት ልደታ በሚገኘው የህዝብ መናፈሻ ጎን ዲቪዥን ጽ/ቤት በመገኘት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡ የክፍያ ሁኔታ በኤሌክትሮኒክስ ማስተላለፍ (አካውንት ቁጥር 1000338000719 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ በዕቃ አቅራቢነት በፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር መመዝገቡን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፣ ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር መለያ ቁጥር (TIN) ሰርተፍኬትና የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ በቅድሚያ በተዘረዘረው መሰረት የጨረታ ማስከበሪያ ቢያንስ ለ90 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ በCPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በኤሌክትሮኒክ ትራንስፈር ለምድብ አንድ ብር 150,000.00 (አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር)፣ ለምድብ ሁለት ብር 100,000.00(አንድ መቶ ሺህ)፣ ለምድብ ሶስት እና አራት ለእያንዳንዳቸው ብር 80,000.00(ሰማንያ ሺህ)፣ ለምድብ አምስት ብር 50,000.00(ሃምሳ ሺህ) ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ይህንን እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ከዋናው ሰነድ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ላሸነፉበት የዕቃ ዝርዝር የጠቅላላ ዋጋውን 10% (የውል ማስከበሪያ) ውል በተፈረመ በ15 ቀናት ውስጥ ማስያዝ ይኖርበታል ፡፡
- የሚገዙ እቃዎችና ተያያዥ አገልግሎቶች መጠን 20% ሊጨምር ወይም 20% ሊቀንስ ይችላል ፡፡
- ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ለ 60 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን አለበት፡፡ ከዚህ ያነሰ የጨረታ ዋጋ ፀንቶ መቆያ ጊዜ ያቀረበ ተጫራች ከጨረታው ይሰረዛል ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን በስሙ ያልገዛ ማንኛውም ተወዳዳሪ በጨረታው መሳተፍ አይችልም፡፡
- ጨረታው ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ/ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዕለቱ ከቀኑ በ 8:30 5ኛ ፎቅ በመ/ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል ፡፡ ከጨረታው መዝጊያ ሰዓትና ቀን ዘግይቶ የሚመጣ ማንኛውም የመወዳደሪያ ሰነድ ተቀባይነት የለውም ፡፡
- ተጫራቾች ዲቪዥን መ/ቤቱ ባስቀመጠው የዋጋ ማቅረቢያ ፎርማት መሰረት ግልጽ በሆነ መልኩ ሞልቶ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ የሚቀርበው ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስን ያካተተ ወይም አለመሆኑን በግልጽ ተለይቶ መቀመጥ አለበት፡፡ ይህንን ያልገለጸ ተወዳዳሪ ያቀረበው ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስን እንዳካተተ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡
- ዲቪዥኑ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ውሃና ሳኒቴሽን መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ዲቪዥን
አድራሻ፡ ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08፣ የቦታው ልዩ ስም፡- ልደታ ኮንደሚኒየም ልደታ መናፈሻ አጠገብ
ስልክቁጥር፡- +251 11 5579512/9036 (1ኛ ፎቅ ግዥ ክፍል)
e-mail- kiyake21@gmail.com
የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ውሃና ፍሳሽ መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ዲቪዥን
✨ messages.ai_summary
Addis Ababa Water and Sewerage Authority's Water and Sanitation Infrastructure Expansion Division seeks suppliers for Toyota and Ford vehicle spare parts, tires and batteries, car decoration materials, and vehicle repair tools, via national open tender. Bidders must be registered with the Ministry of Finance and Economic Development as goods suppliers and submit a renewed business license, TIN, and VAT registration.
