መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር በቅጥር ግቢው ውስጥ የሚገኙትን ያገለገሉ ቁሳቁሶችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ሰነድ ቁጥር 131
መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር በቅጥር ግቢው ውስጥ የሚገኙትን ያገለገሉ ቁሳቁሶችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ቁሳቁሶቹም፡
- አልሙኒየምና እስቴለንስ ስቲል
- የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
- የብረት ገዳዎች (ዲፖዎች) ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶችና ቆባላሪዎች /ስክራፕ/ (ለ2ኛ ጊዜ የወጣ)
- የተነቃቀሉ ጣውላዎች
- የተለያዩ ካሳዎች ከነጠርሙሳቸው
- የተሰባበሩ የፕላስቲክ ወንበሮችና ቁርጥራጭ ፕላስቲክ
- ያገለገሉ ሶፋዎች
- ያገለገሉ የስፖንጅ ፍራሾች
በመሆኑም መጫረት የሚፈልጉ ተጫራቾች አድራሻ፡ አዲስ አበባ ከተማ፣ ለሚኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03፣ (በተለምዶ አያት ኮንዶሚኒየም፣ ከጠበል መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት) በሚገኘው በማዕከሉ ዋና መሥሪያ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ቁሳቁሶቹ በሚገኙበት ቦታ በመገኘት ከተመለከቱ በኋላ በማዕከሉ የጠቅላላ አገልግሎት ክፍል ድረስ በመምጣት ብር 400 (አራት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
የጨረታ ሰነዱ ለሽያጭ የተዘጋጁትን ቁሳቁሶች ዝርዝር የያዘ ሲሆን ዕቃዎቹን እየተዘዋወሩ ከተመለከቱ በኋላ በሰነዱ በእያንዳንዱ ቁጥር አንፃር የተለዩትን ዕቃዎቹን የሚገዙበትን ዋጋ በመሙላት እና ዕቃውን ለመግዛት ያስገቡትን ዋጋ 10% ለጨረታ ማስከበሪያ ከያዘ ሲ.ፒ.ኦ ጋር በማያያዝ ካሸጉ በኋላ የጠቅላላ አገልግሎት ድረስ በመምጣት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀን አየር ላይ ቆይቶ በ11ኛው ቀን ከጧቱ በ4፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ5፡00 ሰዓት ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 11ኛው ቀን እሁድ ወይም ብሔራዊ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
ማሳሰቢያ፡- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0989-90-90-51 ወይንም 0975-26-41-59 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
