Tender Detail

Tender Details

  • Company የጊዶሌ ከተማ አስተዳደር ፋ/ፕ/ል/ጽ/ቤት
  • Address , Phone:
  • Website
  • Deadline16 Oct 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200(ሁለት መቶ ብር)
  • Bid Securityለእያንዳንዱ ጨረታ 25,000 ብር (ሲ.ፒ.ኦ/ በጥሬ ገንዘብ)
  • opening dateበዕለቱ 4:30 ላይ በጊዶሌ ከተማ አስተዳደር ፋ/ፐ/ል/ጽ/ቤት
  • Categories Office Supplies And Services , Stationery Materials , Cloth And Shoes

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋርዱላ ዞን የጊዶሌ ከተማ አስተዳደር ፋ/ፐ/ል/ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ከሚፈፅማቸው ግዥዎች መካከል:- ሎት 1. የጽሕፈት መሣሪያዎችንና ሌሎች ዓላቂ የቢሮ ዕቃዎችን እና ሎት 2. የደንብ ልብስ /የሥራ ልብስ ግዥዎችን ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን ከሚያሟሉ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::

የጊዶሌ ከተማ አስተዳደር ፋ/ፕ/ል/ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋርዱላ ዞን የጊዶሌ ከተማ አስተዳደር ፋ/ፐ/ል/ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ከሚፈፅማቸው ግዥዎች መካከል:-

ሎት 1. የጽሕፈት መሣሪያዎችንና ሌሎች ዓላቂ የቢሮ ዕቃዎችን እና
ሎት 2. የደንብ ልብስ /የሥራ ልብስ ግዥዎችን

ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን ከሚያሟሉ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል:: ስለዚህ:-

  • በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው::
  • የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ::
  • የአቅራቢዎች ምዝገባ የምስክር ወረቀት /ኦን ላይን/ ያላቸው::
  • የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN No/ ያላቸው::
  • የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ጨረታ 25,000 ብር ከታወቀ ባንክ ሲ.ፒ.ኦ/ በጥሬ ገንዘብ ማቅረብ የሚችሉ::
  • ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከጊዶሌ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቅ/ጽ/ቤት በመቅረብ ለአንዱ ጨረታ የማይመለስ 200 ብር በመክፈል መግዛት አለባቸው::
  • የገዙትንም ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ በማዘጋጀት በሁለት የተለያዩ በታሸገ ፖስታ በማሸግ ኦርጅናሉ ላይ ኦርጅናል ኮፒው ላይ ኮፒ ብሎ በመፃፍ ፊርማና ማህተም በማሳረፍ ይህ ማስታወቂያ በዚህ ጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ እስከ 15ኛው ቀን 4:00 ሰዓት ብቻ ማስገባት አለባቸው 15ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል:: ጨረታው በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4:30 ላይ በጊዶሌ ከተማ አስተዳደር ፋ/ፐ/ል/ጽ/ቤት ይከፈታል::
  • ተጫራቾች በሰዓቱ ያለመገኘት የጨረታውን አከፋፈት አያስተጓጉልም::
  • የጨረታው አሸናፊዎች ተለይተው ከተገለጸ ከ7 ቀናት በኋላ በ5 ቀናት ውስጥ አሸናፊዎች የውል ማስከበሪያ 10% በማስያዝ ውል መግባት አለባቸው:: ተሸናፊዎች ደግሞ ያስያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ መውሰድ ይችላሉ::
  • አሸናፊዎች በገቡት ውል መሠረት ዕቃዎቹን እስከ ጊዶሌ ከተማ አስተዳደር ፋ/ፐ/ል/ጽ/ቤት ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው::
  • በጨረታ ሰነድ ላይ የተሞሉ ዋጋዎች እስከ 40 ቀናት ድረስ ፀንተው መቆየት ይኖርባቸዋል።
  • መ/ቤቱ ከጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ለተጨማሪ መረጃ:- ስልክ 0467740564/536 ይደውሉ

የጊዶሌ ከተማ አስተዳደር ፋ/ፕ/ል/ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Gidole Town Administration invites suppliers to bid for Lot 1: stationery and other office supplies, and Lot 2: uniforms/work clothing. Eligible bidders must have a renewed trade license, VAT registration, supplier registration certificate, and TIN.
Save Tender