Tender Detail

Tender Details

  • Company በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ት/ጽ/ቤት የሐምሴ የሐምሌ 19/67 የመጀ/ደ/ት/ቤት
  • Address , Phone: 0111-27-53-72
  • Website
  • Deadline10 Oct 2026, 5:30 PM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price200.00 (ሁለት መቶ ብር)
  • Bid Securityበሎት (ሲ.ፒ.ኦ): ሎት1 ብር 20,000.00፣ ሎት2 ብር 12,000.00፣ ሎት3 ብር 5,000.00፣ ሎት4 ብር 10,000.00፣ ሎት5 ብር 12,000.00፣ ሎት6 ብር 942.26፣ ሎት7 ብር 5,000.00፣ ሎት8 15,000.00፣ ሎት9 ብር 18,219.62
  • opening dateበ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተቋሙ ፋይናንስ ቢሮ ይከፈታል
  • Categories Catering And Cafeteria Services , Furniture , Cloth And Shoes

የደንብ ልብስ እና ስፌት፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ የህትመት ስራ፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ ቋሚ ዕቃዎች፣ የመስተንግዶ አገልግሎት እና ሌሎች ግዥ - የሐምሌ 19/67 ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት (ጉለሌ ወረዳ 7)

በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ት/ጽ/ቤት የሐምሴ የሐምሌ 19/67 የመጀ/ደ/ት/ቤት


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 001/2019

በጉለሌ ክ/ከ በወረዳ 7 አስ/ስር የሚገኘው የሐምሌ 19/67 ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በመደበኛ እና በውስጥ ገቢ በጀት በግልፅ ጨረታ ከዚህ በታች ባለው ሎት መሠረት

ሎት1.የደንብ ልብስ እና ስፌት
ሎት 2. አላቂ የቢሮ እቃዎች
ሎት 3.የህትመት ስራ
ሎት 4. የትምህርት መርጃ መሳሪያዎች
ሎት 5. የፅዳት ዕቃዎች
ሎት 6. የማሽነሪ ጥገና እና ሰርቪስ (ኮምፒዩተር፣ ፕሪንተር፣ ፎቶኮፒ ማሽን እና ማባዣ ማሽን)
ሎት7. የህንፃ የኤሌክትሪክ፣ የቧንቧ ዕቃዎች እና ተገጣጣሚ፣ የጥገና እና የቀለም ቅብ ስራ
ሎት 8. ቋሚ ዕቃዎች
ሎት9. የመስተንግዶ አገልግሎት ግዥ ለመግዛት በጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል፡፡

በዚህም መሰረት በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለፀውን መስፈርት በማየት የምትወዳደሩ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

  • የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያለው
  • በገንዘብ ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር መ/ቤት በአቅራቢዎች /ዘርፉ የተሰማራበት/ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ
  • ጨረታውን ለመሳተፍ በቅድሚያ የማይመለስ ብር በጥቅል 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ተቋሙ ፋይናንስ ቢሮ በመቅረብ መግዛት የምትችሉ ሆኑን እንገልጻለን፡፡
  • ጨረታውን መወዳደር የሚችሉ ጥቃቅን እና አነስተኛ ኢ/ፕራይዝ እሴት የሚጨምሩ /አምራች/ ሆነው ከአደራጃቸው ተቋም በሚፅፍላቸው ደብዳቤ መሰረት ያለከፍያ መጫረት ይችላሉ፡፡
  • ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዶቻቸውን ኦሪጅናል እና ፎቶ ኮፒ ሰነድ ለየብቻው በታሸገ ኤንቬሎፕ አድርገው ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የሚቀርበው ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆኑን በግልፅ መቀመጥ አለበት፡፡
  • ጫራቾች ለሚያቀርቧቸው ዕቃዎች ከጨረታው መክፈቻ ቀን በፊት ናሙና የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
  • ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው እቃዎች በሎት 1.ብር 20,000.00፣ ሎት2.ብር 12,000.00፣ ሎት 3. ብር 5,000.00፣ ሎት4. ብር 10,000.00፣ ሎት5. ብር 12,000.00፣ ሎት 6. ብር 942.26፣ ሎት7. ብር 5,000.00፣ ሎት8. 15,000.00፣ ሎት 9. ብር 18,219.62 የጨረታ ዋስትና ቢያንስ ለስድስት ወር ፀንቶ የሚቆይ በባንክ የተረጋገጠ የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ እስከ ጨረታ መዝጊያው ቀን ድረስ ከዋና ሰነድ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  • ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት እስከ 10 ተከታታይ የስራ ቀን ድረስ የሚቆይ ሆኖ ከቀኑ 11:30 ታሽጎ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተቋሙ ፋይናንስ ቢሮ ይከፈታል፡፡ የጨረታው አሸናፊ ተጫራች ውል ከመዋዋሉ በፊት የጨረታ ማስከበሪያ 10% ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ አለበት፡፡
  • አሸናፊው ተጫራች የተገዙትን እቃዎች በራሱ ትራንስፖርት ተቋሙ ድረስ በማቅረብ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡

ማሳሰቢያ:- መስሪያ ቤቱ በጨረታ ሰነድ ውስጥ የተጠቀሱትን እቃዎች ካለው በጀትና (የተሻለ መንገድ ካገኘ) እንዲሁም በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ የዕቃዎን 20% የመጨመር፣መቀነስ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡

አድራሻ:- ጉለሌ ክፍለ ከተማ ከአዲሱ ገበያ ከፍ ብሎ ወረዳ 7 አስተዳደር ጽ/ቤት አጠገብ ሆኖ ወደ ውስጥ 50ሜትር ገባ ብሎ ይገኛል፡፡

ለበለጠ መረጃ:- በስልክ ቁጥር 011-154-69-29 ወይም 011-127-53-72 ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡

በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ት/ጽ/ቤት ስር የሐምሌ 19/67 ቅድመ አንደኛ፤ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት

✨ messages.ai_summary
The school seeks suppliers for uniforms and tailoring, consumable office items, printing, teaching aids, cleaning supplies, machine maintenance (computers, printers, copiers), building electrical, plumbing and painting works, furniture, and catering services. Bidders need a renewed trade license, supplier registration, and TIN/VAT registration.
Save Tender