የተቃጠሉ ዘይቶች ሽያጭ - ሚድሮክ ኮንስትራክሽን ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
ሚድሮክ ኮንስትራክሽን ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
ሚድሮክ ኮንስትራክሽን ኢትዮጵያ ኃ.የተ.የግል.ማህበር
MIDROC Construction Ethiopia PLC
Document No: MCE/FORM/5/348
አስቸኳይ የጨረታ ማስታወቂያ
የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ አባል የሆነው ድርጅታችን ሚድሮክ ኮንስትራክሽን ኢትዮጵያ ኃላ/የተወሰነ የግል ማህበር ለሥራ አገልግሎት ሲጠቀምባቸው የነበሩ የተቃጠሉ ዘይቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::
በዚሁ መሠረት፡-
- ተጫራቾች አዲስ አበባ፣ልደታ ክፍለ ከተማ፣ወረዳ 08 ከመካኒሣ አቦ ቤተክርስቲያን ከፍ ብሎ ከኩዊንስ ሱፐርማርኬት ቀጥሎ ባለው የኢትዮ አግሪሴፍት ቅጥር ግቢ ውስጥ በሚገኘው የድርጅታችን ዋና መስሪያ ቤት በሚገኘው ህንፃ 3ኛ ፎቅ የድርጅቱ ንብረት አስተዳደር ቢሮ በአካል በመቅረብ የምትወዳደሩበትን የአንድ ሊትር ዋጋ ከቫት በፊት ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን::
- በጨረታው ለመሣተፍ ግለሰብ ወይም ድርጅት መሆን ይችላል::በጨረታ የሚሣተፈው ድርጅትም ሆነ ግለሰብ ከፌዴራል አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የተቃጠለ ዘይት የመሰብሰብ፣የማጓጓዝ፣መልሶ ጥቅም ላይ የማዋል (Recycling) ፍቃድና የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
- በጨረታው ለመሣተፍ በኢትዮጵያ ውስጥ የተቋቋመ ድርጅትና በበጀት ዓመቱ ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰነድ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰነድና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች በጨረታው ለሚሳተፉባቸው የተቃጠሉ ዘይቶች ለጨረታ ያቀረቡትን ጥቅል ዋጋ 10%የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ/CPO/ በሚድሮክ ኮንስትራክሽን ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ስም ማሰያዝ ይኖርባቸዋል፤
- ተጫራቾች ቃሊቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ከመስከረም 20 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ.ም ባሉት ስድስት የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት የተቃጠለ ዘይቱን በአካል በመገኘት ማየት ይችላሉ፤
- ተጫራቾች የሚገዙበትን የተቃጠሉ ዘይቶች የአንድ ሊትር ዋጋ ከቫት በፊት በመጥቀስ ጨረታው በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰአት ከመስከረም 20 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ.ም ጠዋት ረፋድ 4:00 ድረስ ከላይ በተጠቀሰው የድርጅቱ አድራሻ የንብረት አስተዳደር ቢሮ በመቅረብ የዋጋ ማቅረቢያና ሲፒኦ በስም በታሸገ ፖስታ በማዘጋጀት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ በማስገባት መወዳደር ይችላሉ:: ጨረታው መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ.ም ጠዋት ከረፋዱ 4:00 ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ዕለት ጠዋት ከረፋዱ 4:30 ይከፈታል::
- በጨረታው አሸናፊ የሆነ ግለሰብ /ድርጅት/አሸናፊነቱ በተገለጸለት በ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ጊዜ ውስጥ አሸናፊ የሆነበትን የተቃጠለ ዘይት )ሙሉ ዋጋ ገቢ በማድረግ ንብረቱን ማንሳት ሲኖርበት ማንሳት ካልቻለ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው CPO የማይመለስ ይሆናል ::
- አሸናፊ ድርጅት/ግለሰብ/ የተቃጠለ ዘይቱን የመጫን የማጓጓዝ እና ሌሎች ተዛማጅ ወጪዎችን በራሱ ይሸፍናል::
- በጨረታው የተሸነፈ ተጫራች ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ CPO ለተጫራች እንዲመለስ ይደረጋል፡
- ሻጭ ድርጅት የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብት አለው::
አድራሻ፡-ልደታ ክፍለ ከተማ መካኒሣ አቦ ቤተክርስቲያን ከፍ ብሎ ኢትዮ አግሪሴፍት ቅጥር ግቢ ውስጥ
ማሳሳቢያ፡
- ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር +251 911127478/+251 911900960 /+251919487762 ይጠቀሙ::
- ተጫራቾች ሙሉ አድራሻ እና አማራጭ ስልኮቻቸውን መጥቀስ ይኖርባቸዋል::
ሚድሮክ ኮንስትራክሽን ኢትዮጵያ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር
✨ messages.ai_summary
MIDROC Construction Ethiopia is selling used burnt oil via open bid. Individuals or companies may participate. Bidders must hold a federal environmental protection license for collecting, transporting, and recycling burnt oil, plus a renewed trade license, TIN, VAT registration, and proof of tax payment.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
