በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ እውቀት ወጋገን ቅድመ መጀመሪያና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የ2019 ዓ.ም በጅት ዓመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ እውቀት ወጋገን የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2019 ዓ.ም
በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ እውቀት ወጋገን ቅድመ መጀመሪያና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የ2019 ዓ.ም በጅት ዓመት
| ሎት 1. የደንብ ልብስ | ሎት 6. አላቂ የጽዳት እቃ |
| ሎት 2. አላቂ የቢሮ እቃ | ሎት 7. ልዩልዩ መሳርያዎች |
| ሎት 3. የህትመት አገልግሎት | ሎት 8. ቋሚ እቃዎች |
| ሎት 4. አላቂ የህክምና እቃዎች | ሎት 9. የኤልክትሮኒክስ ጥገና |
| ሎት 5. አላቂ የትምህርት እቃ | ሎት 10. ለቁሳቁስና እና ተገጣጣሚዎች |
በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ስለሆንም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች
- ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ ተጫራቾች በመንግስት አቅራቢነት የተመዘገቡበትን የሚያቀርቡ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የሰነድ ማስረጃዎችን ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ የሚችሉና ቋሚ ዕቃዎችን ገዥው መስሪያ ቤት ድርጅታችሁ በአካል መተው ለማየት ከፈለገ ለመተባበር ፈቃደኛ ሊሆኑ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት የሚችሉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር ብቻ/በመክፈል በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ እውቀት ወጋገን የመጀ/ደ/ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 8 በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከ2፡30 እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ዋናውና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ አሽጎ ት/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ትቤ/ቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ ሲሆን ጨረታው በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰአት ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ትምህርት ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ
ሎት 1. የደንብ ልብስ 12850.74 ሎት 2. አላቂ የቢሮ እቃ 6000.57 ሎት 3. የህትመት አገልግሎት 375.00 ሎት 4. አላቂ የህክምና እቃዎች 450.00 ሎት 5. አለቂ የትምህርተ እቃ 7417.05 ሎት 6. አላቂ የጽዳት እቃ 9000.00 ሎት 7. ልዩልዩ መሳርያዎች 1200.00 ሎት 8. ቋሚ እቃዎች 7500.00 ሎት 9. የኤልክትሮኒክስ ጥገና 750.00 ሎት 10. ለቁሳቁስና እና ተገጣጣሚዎች 1258.02 - የውል ማስከበርያ ጨረታ ያሸነፉበትን 10% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በመስሪያ ቤቱ ስም ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን እቃ በሙሉ ትቤ/ቱ ንብረት ክፍል በራሳቸው ትራንስፖርት ማቅረብ አለበት፡፡
- የቋሚ እቃዎችን መስሪያ ቤቱ ድረስ ሳጥል ማምጣት የማይችሉበትን በፎቶ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ናሙናው የሚቀርብባቸውን እቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ተጠናቆ መግባተ አለባቸው፡፡
- በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ እራሳቸው አምርተው ለገበያ የሚያቀርቡትን እቃ እና በሀገር ውስጥ ምርቶች ብቻ መወዳደር እንደሚችሉ
አድራሻ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የእውቀት ወጋገን የመ/ጀ/ደ/ት/ቤት ልዩ ቦታው ሳሪስ የቀድሞ ዘንባባ ጀነራል ሆስፒታል ገባ ብሎ ይገኛል፡፡
ስልክ ቁጥር፡ 0114707891 0114407155
በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ እውቀት ወጋገን ቅድመ መጀመሪያና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት
✨ messages.ai_summary
The school seeks suppliers for 10 lots including uniforms, office and cleaning supplies, printing, medical and educational materials, equipment, furniture, and electronics repair. Bidders need a renewed business license, tax clearance, government supplier registration, VAT registration, and must submit samples. Local producers of domestic goods may compete.
