Tender Detail

Tender Details

  • Company በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጃንሜዳ ጤና ጣቢያ
  • Address ከ6ኪሎ ወደ ጃንሜዳ የሚወስደው መንገድ ከቴሌው ፊት ለፊት ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0111261509
  • Website
  • Deadline07 Oct 2026, 10:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price300
  • Bid Securityበሎት: ከብር 2,000 እስከ 20,000 (CPO / BID BOND)
  • opening dateበ10ኛው የስራ ቀን በ4:30 ሰዓት (ከጠዋቱ 10:30 AM)
  • Categories Office And Home Furniture , Stationery Materials , Cloth And Shoes

የደንብ ልብስ፣ የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የቢሮ እና የህክምና እቃዎች፣ ጥገና እና ልዩ ልዩ መሳሪያዎች ግዥ - አራዳ ክፍለ ከተማ ጃንሜዳ ጤና ጣቢያ (ጨረታ ቁጥር 001/2019)

በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጃንሜዳ ጤና ጣቢያ


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር 001/2019

በአራዳ ክፍለ ከተማ ጃንሜዳ ጤና ጣቢያ በ2019 በጀት ዓመት 1ኛ ዙር ጨረታ ቁጥር 001/2019 ለጤና ጣቢያው አገልግሎት የሚውሉ ደንብ ልብስ፣ የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የፅዳት እቃዎች፣ ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣ አላቂ የህክምና እቃዎች፣ ቋሚ የህክምና እቃዎች የጥገና፣ ህትመት ፣ የጥገና ዕቃዎች፣ የፈሳሽ ቆሻሻ ማንሳት የላውንደሪ ማሽን ጥገና፣ የጀኔሬተር ጥገና ፣የሚወገዱ መድሃኒቶች እና ልዩ ልዩ መሳሪያዎች በግልፅ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት መጫረት የምትፈልጉ ተጫራቾች

  1. በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ያላችሁ
  2. በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገባችሁ
  3. የታደሰ ህጋዊ ፍቃድ ወይም የዘመኑን ግብር ከፋይ የሆናችሁ
  4. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆናችሁ
  5. ጨረታ ሰነድ ዋጋ ብር 300.00 ብር /ሶስት መቶ ብር ብቻ/
  6. የጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ ብር
    ሎትየገንዘብ መጠን
    ሎት 1 የደንብ ልብስ13,000.00
    ሎት 2 አላቂ የቢሮ እቃዎች10,000.00
    ህትመት9,000.00
    ሎት 3 አላቂ የህክምና እቃዎች5,000.00
    ሎት 4 የፅዳት እቃዎች2,000.00
    ሎት 5 ቋሚ የቢሮ እቃዎች20,000.00
    ሎት 6 የጥገና እቃዎች5,000.00
    ሎት 7 የጀኔሬተር ጥገና10,000.00
    ሎት 8 የላውንደሪ ማሽን ጥገና10,000.00
    ሎት 9 የፈሳሽ ቆሻሻ ማንሳት10,000.00
    ሎት 10 ቋሚ የህክምና እቃዎች ጥገና10,000.00
    ሎት 11 ል ልዩ መሳሪያዎች2,000.00
    ሎት 12 የሚወገዱ መድሃኒቶች5,000.00

    በዚሁ መሰረት በጃንሜዳ ጤና ጣቢያ ስም በባንክ የተመሰከረለት CPO እና BID BOND ማስያዝ የሚችል ብቻ

  7. ተጫራቾች የሚያስገቡት ዋጋ VAT 15% ያካተተ መሆን ይኖርበታል።
  8. ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ማቅረቢያ ጊዜ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ቀናት በጃንሜዳ ጤና ጣቢያ ውስጥ በፋይናንስ ክፍል ቢሮ ቁጥር 226 በመግዛት በታሸገ ፖስታ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በ10ኛው የስራ ቀን በ4:00 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ በ4:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውን በተገኙበት የጨረታ ሰነዱ ይከፈታል።
  9. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  10. ተጫራቾች ያሸነፉበትን እቃዎች ጃንሜዳ ጤና ጣቢያ ንብረት ክፍል ውስጥ ሙሉ ወጪውን ችለው ማስረከብ አለባቸው።
  11. ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ ይኖርበታል ማቅረብ ለማይችሉት በፎቶ ማቅረብ ይኖርበታል።
  12. ፋይናንሻል ኦርጅናል ፋይናንሻል ኮፒ ማቅረብ ይኖርበታል።
  13. ለበለጠ መረጃ ዝርዝር መረጃ ሰነድ ላይ መመልከት ይችላሉ።

አድራሻ :- ከ6 ኪሎ ወደ ጃንሜዳ የሚወስደው መንገድ ከቴሌው ፊት ለፊት አራዳ ክፍለ ከተማ ጃንሜዳ ጤና ጣቢያ ሲሆን ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0111261509/ 0111261961 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል።

በአራዳ ክፍለ ከተማ የጃንሜዳ ጤና ጣቢያ

✨ messages.ai_summary
Janmeda Health Station seeks suppliers for uniforms, stationery, cleaning supplies, office and medical equipment, printing, and maintenance services including generator, laundry machine, and liquid waste removal, plus expired medicines and miscellaneous tools. Bidders must be licensed, registered, tax-compliant, and VAT-registered.
Save Tender