Tender Detail

Tender Details

  • Company በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን መስተዳድር የሲያደብር እና ዋዩ ወረዳ ፍ/ቤት
  • Address , Phone:
  • Website
  • Deadline07 Oct 2026, 10:00 PM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceሎት 1፡ ብር 250፤ ሎት 2-6፡ ብር 200 (በሎት)
  • Bid Securityየእቃው ጠቅላላ ዋጋ 1% (ሲፒኦ፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ)
  • opening dateበ11 ኛው ቀን በእለቱ ከጠዋቱ በ4፡30 ይከፈታል
  • Categories Cleaning And Janitorial Equipment , Stationery Materials , Electronics Materials

የፅህፈት መሳሪያ፣ የህትመት፣ የፅዳት፣ ኤሌክትሮኒክስ እና የቋሚ እቃዎች ግዢ - የሲያደብር እና ዋዩ ወረዳ ፍ/ቤት

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን መስተዳድር የሲያደብር እና ዋዩ ወረዳ ፍ/ቤት


ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በአብክመ ሰ/ሸዋ ዞን መስተዳድር የሲ/ዋ/ወ/ፍ/ቤት የ2019 በጀት አመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ፡፡ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማለትም

  • ሎት 1፡- አላቂ የፅህፈት መሳሪያዎች የፐሪንተር ቀለም፣የፎቶ ኮፒ ቀለሞችና ልዩ ልዩ የስቴሽነሪ እቃዎች የሰነድ መሸጫ ዋጋ ብር 250 /ሁለት መቶ ሃምሳ ብር ብቻ/
  • ሎት 2፡- የህትመት እቃዎች የሰነድ መሸጫ ዋጋ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ ብቻ
  • ሎት 3፡- የፅዳት እቃዎች የሰነድ መሸጫ ዋጋ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ ብቻ
  • ሎት 4፡- የቋሚ አላቂ እቃዎች የሰነድ መሸጫ ዋጋ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ ብቻ
  • ሎት 5፡- ኤሌክትሮኒክስ የሰነድ መሸጫ ዋጋ ብር 200/ሁለት መቶ ብር ብቻ/
  • ሎት 6፡- የቋሚ እቃዎች የሰነድ መሸጫ ዋጋ ብር 200/ሁለት መቶ ብር ብቻ/ ሲሆን
  1. የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/TIN/ ያላቸው፡፡
  3. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 6 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸው ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከማጫረቻ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የሚገዙ እቃዎችን አይነት ከጨረታው ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከላይ በተገለፀው መሰረት የሰነዱን ዋጋ በመክፈል ከግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 17 ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የእቃው ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡ የተጭበረበረ ሲፒኦ/ የባንክ ዋስትና ማቅረብ በህግ ያስቀጣል፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሀሳቡን/የማጫረቻ ሰነዱን/ ኦርጅናል ሰነድ ብር ካለምንም ስርዝ ድልዝ በጥንቃቄ በመሙላት አንድ ወጥ በሆነ በታሸገ ፖስታ የሚሳተፉበትን የጨረታ አይነት በፖስታው የውጭ ክፍል ላይ በመፃፍ በግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስ ሂደት ቢሮ ቁጥር 13 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  9. ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ በ11 ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ተዘግቶ በእለቱ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፡፡ የበአል/እረፍት/ ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀናትና በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል፡፡
  10. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፉ ከተረጋገጠ በኋላ የውል ማስከበሪያ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ10% ከተጨማሪ እሴት ታክስ ጋር በባንክ በተመሰከረ ትክክለኛ ሲፒኦ በማስያዝ ውል መፈፀም ይኖርበታል፡፡
  11. መ/ቤቱ በግዢ ላይ 20% የመጨመር እና የመቀነስ መብት አለው፡፡
  12. የጨረታ ውድድሩ በጥቅል ዋጋ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡
  13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. አድራሻ፡ የሲ/ዋ/ወ/ፍ/ቤት ከአዲስ አበባ በደ/ብርሃን መስመር ከደብረ ብርሃን ከተማ ወደ ጅሩ በሚወስደው መንገድ ላይ 46 ኪ.ሜ ከተጓዙ በኋላ ይገኛል፡፡
  15. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0116200671/0116200014/219/ መጠየቅ ይቻላል፡፡

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን መስተዳድር የሲያደብር እና ዋዩ ወረዳ ፍ/ቤት

✨ messages.ai_summary
The Siya Debir and Wayu Woreda Court seeks suppliers for stationery, printing, cleaning, electronics, and fixed assets across six lots. Bidders need a renewed trade license, TIN, and VAT registration proof. The contract is lump-sum, and the court may adjust quantities by 20%.
Save Tender