Tender Detail

Tender Details

  • Company Kombolcha Textile Share Company (ኮምቦልቻ ጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበር)
  • Address አማራ ክልል ኮምቦልቻ (ወሎ) በዋናው መስሪያ ቤት እና ራስ ደስታ ዳምጠው ጎዳና ፓፓሲኖስ ህንጻ 1ኛ ፎቅ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-5530124
  • Websitehttps://kombolchatextile.com/
  • Deadline10 Oct 2026, 5:00 PM
  • magazineADDIS ZEMEN
  • Bid Document Price200
  • Bid Securityበጨረታ መመሪያው ላይ የተገለጸው (በጥሬ ገንዘብ ወይም CPO)
  • opening dateጨረታው በተዘጋ በ3ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰአት (10:00 AM) ኮምቦልቻ ዋናው መ/ቤት; የህዝብ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን
  • Categories Plastic Raw Materials And Products , Textile, Garment & Leather , Steel, Metals And Aluminium

የጨርቅና ክር ተረፈ ምርቶች፣ የጥጥ ቅሪቶች፣ ብረታ ብረትና የፕላስቲክ ጀሪካን/የብረት በርሜል ሽያጭ ጨረታ - ኮምቦልቻ ጨርቃ ጨርቅ አክሲዮን ማህበር

Kombolcha Textile Share Company (ኮምቦልቻ ጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበር)


የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 033/2019

የኮምቦልቻ ጨርቃ ጨርቅ አክሲዮን ማህበር ዝርዝራቸው ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ ዕቃዎች በዝግ ጨረታ መሠረት አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

  1. የተለያዩ መጠን ያላቸው የተጠናቀቁ የጨርቅ እና ክር ተረፈ ምርቶች
  2. የተለያዩ አይነት የጥጥ ቅሪቶችና ተረፈ ምርቶች
  3. የተለያዩ አይነት ብረታ ብረት እና መለዋወጫ ዕቃዎች
  4. የተለያዩ መጠን ያላቸው የተጋቡ የፕላስቲክ ጀሪካኖችና የብረት በርሜሎች እንዲሁም ሌሎች ልዩ ልዩ ዕቃዎች

በጨረታው ማንኛውም በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለው ግለሰብ ወይም ድርጅት መሣተፍ የሚችል ሲሆን ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ከአክሲዮን ማህበሩ ቅ/ጽ/ቤት አዲስ አበባ ወይም ከዋናው መ/ቤት ኮምቦልቻ መግዛት ይችላሉ፡፡

ዕቃዎቹን ዘወትር በስራ ሰአት ( ከሰኞ - አርብ ከ 2:00 እስከ 10:00 እና ቅዳሜ ከ2:00-6:00) ዋናው መ/ቤት ኮምቦልቻ በመመልከት የሚገዙበትን ነጠላ ዋጋ ማህበሩ ባዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ በትክክል በመሙላት በስም በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በጨረታ መመሪያው ላይ የተገለጸውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ወይም በ (CPO) በማስያዝ ከላይ በተገለጹት ቦታዎች ላይ በመገኘት ዋጋ ማቅረብ የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ጨረታው ማስታወቂያው በተዘጋ በ3ኛው ቀን ኮምቦልቻ /ወሎ/ በሚገኘው በዋናው መ/ቤት ከጠዋቱ 4:00 ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን የህዝብ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል፡፡

አ/ማህበሩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታው በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ

ስልክ ቁጥር 033-5510627 / 5510211 (ኮምቦልቻ)
ስልክ ቁጥር 011-5511805 / 5530124 (አዲስ አበባ)
ራስ ደስታ ዳምጠው ጎዳና ፓፓሲኖስ ህንጻ 1ኛ ፎቅ

ኮምቦልቻ ጨርቃ ጨርቅ አክሲዮን ማህበር

✨ messages.ai_summary
Kombolcha Textile Share Company invites sealed bids for the sale of various textile and yarn remnants, cotton waste, assorted metal items and spare parts, plastic jerricans and metal barrels, and other miscellaneous goods. Open to any individual or firm with a valid trade license.
Save Tender