የኮምቦልቻ ጨርቃ ጨርቅ አክሲዮን ማህበር ዝርዝራቸው ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ መሠረት አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
የኮምቦልቻ ጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበር
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 033/2019
የኮምቦልቻ ጨርቃ ጨርቅ አክሲዮን ማህበር ዝርዝራቸው ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ መሠረት አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
- የተከማቹ መጠን ያላቸው የተጠናቀቁ የጨርቅ እና ከር ተረፈ ምርቶች
- የተለያዩ አይነት የጥጥ ቅሪቶችና ተረፈ ምርቶች
- የተለያዩ አይነት ብረታ ብረት እና መለዋወጫ ዕቃዎች
- የተለያዩ መጠን ያላቸው የተጋቡ የፕላስቲክ ጀሪካኖችና የብረት በርሜሎች እንዲሁም ሌሎች ልዩ ልዩ ዕቃዎች
በጨረታው ማንኛውም በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለው ግለሰብ ወይም ድርጅት መሳተፍ የሚችል ሲሆን ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ከአክሲዮን ማህበሩ ቅ/ጽ/ቤት አዲስ አበባ ወይም ከዋናው መ/ቤት ኮምቦልቻ መግዛት ይችላሉ፡፡
እቃዎቹን ዘወትር በስራ ሰዓት (ከሰኞ - አርብ ከ2፡00 እስከ 10፡00 እና ቅዳሜ 12:00 - 6:00) ዋናው መ/ቤት ኮምቦልቻ በመመልከት የሚገዙበትን ነጠላ ዋጋ እ/ማህበሩ ባዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ በትክክል በመሙላት በሰም በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በጨረታ መመሪያው ላይ የተገለጸውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ወይም በ (CPO) በማስያዝ ከላይ በተገለጹት ቦታዎች ላይ በመገኘት ዋጋ ማቅረብ የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
ጨረታው ማስታወቂያው በተዘጋ በ3ኛው ቀን ኮምቦልቻ /ወሎ/ በሚገኘው በዋናው መ/ቤት ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን የህዝብ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል፡፡
እ/ማህበሩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታው በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ
ስልክ ቁጥር 033-5510627 / 5510211 (ኮምቦልቻ)
ስልክ ቁጥር 011-5511805 / 5530124 (አዲስ አበባ)
ራስ ደስታ ዳምጠው ጎዳና ፓፓሲኖስ ህንጻ 1ኛ ፎቅ
ኮምቦልቻ ጨርቃ ጨርቅ አክሲዮን ማህበር
