በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የገቢዎች ሚኒስቴር አዳማ ቅ/ጽ/ቤት በታክስ ዕዳ የያዛቸውን ለቆዳ ማምረቻ የተዘጋጀውን ህንጻ ለመሸጥ የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
የገቢዎች ሚኒስቴር አዳማ ቅ/ጽ/ቤት
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁ.04/2017
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የገቢዎች ሚኒስቴር አዳማ ቅ/ጽ/ቤት በታክስ ዕዳ የያዛቸውን ለቆዳ ማምረቻ የተዘጋጀውን ህንጻ ለመሸጥ የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁ.04/2017 የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ግብር ከፋዮች የሚጠበቅባቸውን የታክስ ዕዳ በታክስ ህጉ በተፈቀደው የጊዜ ገደብ ባለመክፈላቸው በታክስ አከፋፈል አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀፅ 41 በተሰጠው ስልጣን መሠረት ጂዲ ኢንተርናሽናል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተያዘ ህንጻ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
- በግልጽ ጨረታው የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ማንነቱን የሚገልጽ የነዋሪነት መታወቂያ (ፓስፖርት) ኮፒ ከጨረታ ሰነድ ጋር እያያዘ በኢንቨሎፕ በማሸግ በግልጽ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ የግልጽ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡00 ሰዓት - 11፡00 ሰዓት እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00 - 6፡00 ሰዓት ከቴሌ ከፍ ብሎ ቅ/ጽ/ቤቱ አዲሱ ባስገነባው ህንጻ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 403 ከግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቢሮ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይኖርቦታል፡፡
- በግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ንብረቶች የሰጡትን ዋጋ ሰላኛውን ብቻ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) በገቢዎች ሚኒስቴር አዳማ ቅ/ጽ/ቤት ስም (Ministry of Revenue Adama Branch Office) በባንክ አሰርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቶች የሚከተለው የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሰረት ሰነድ ገዝተው መጫረት ይችላሉ።
ተ.ቁ የመ/ቤቱ የንብረት ዓይነት ለጨረታ የቀረበው የንብረቶቹ መመልከቻ የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት 1 ገቢዎች ሚኒስቴር አዳማ ቅርንጫፍ የቆዳ ማምረቻ ተዘጋጃ ህንጻ 17,514.00 ካሬ ላይ ያረፈ. ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጠበት ቀን ጀምሮ ለ15 ቀናት ማስታወቂያው በጋዜጣ ወጥቶ 15 ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ቀጥሎ ባለው 16ኛ ቀን 3፡45 ተዘግቶ በዚያው ቀን በ4፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡ - የጨረታ መከፈቻ ቦታ፡- በገቢዎች ሚኒስቴር አዳማ ቅ/ጽ/ቤት ከቴሌ ከፍ ብሎ ባስገነባው አዲሱ ህንጻ 4ኛ ፎቅ ከግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳዳር ቢሮ ቁጥር 403 ሲሆን ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም ታዛቢዎች ባሉበት ይከፈታል፡፡
- የግልጽ ጨረታው መከፈቻና መዝጊያ 16ኛው ቀን የመ/ቤቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን የግልጽ ጨረታው መከፈቻና መዝጊያ ቀን ይሆናል፡፡
- ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ያስያዙት (CPO) ከሚከፈሉት ዋጋ ጋር እንደ አስፈላጊነቱ የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቶች ደግሞ የግልጽ ጨረታ ኮሚቴው መረጃውን አጣርቶ እንደጨረሰ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
- የህንጻ ጨረታ ለሚያሸንፉ ተጫራቾች ከስመ-ንብረት ንብረት ዝውውር ጋር ተያያዥነት ላቸውን ወጪዎች ሻጭን አይመለከትም፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀናት ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ ቅ/ጽ/ቤቱ በሚሰጠው አድራሻ ገቢ በማድረግ ሀብት/ንብረት መረከብ ይኖርበታል፡፡
- ከላይ በተ.ቁ 9 በተገለጸው ቀናት ውስጥ ከፍያውን ገቢ በማድረግ ንብረታቸውን ያልተረከቡ ተጫራቾች የግልጽ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በ CPO ያስያዙት የዋስትና ገንዘብ ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ንብረቱ ተቆጥሮ በቀጣይ በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
- ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ የግልጽ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር፡- 022-21-1873/ 022-211-1728 እና 022-211-0762 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
ገቢዎች ሚኒስቴር አዳማ ቅ/ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Ethiopia's Ministry of Revenue Adama branch is selling by open bid a building prepared for leather manufacturing, seized for tax debt. Bidders must submit ID copies and a CPO; transfer costs are the buyer's. The branch may cancel the bid.
Not stated in the notice: bid security. Check the original document or ask the issuer.
