Tender Detail

Tender Details

  • Company የከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ማዕከል
  • Address ገላን : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-4-39-76-61
  • Website
  • Deadline06 Oct 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ለእያንዳንዱ ሰነድ
  • Bid Securityብር 50,000.00 (ሀምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረለት ሲ.ፒ.ኦ
  • opening dateበዕለቱ በ4፡15 ሰዓት
  • Categories Furniture And Furnishing , Textile, Garment & Leather , Animals , Animal Feed And Supply

የከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ማዕከል በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው ድርጅት ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

የከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ማዕከል


የጨረታ ማስታወቂያ

የከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ማዕከል

ጨረታ ቁጥር (1) ለእንጨትና ብረታ ብረት ለትምህርትና ስልጠና ስራዎች አገልግሎት የሚውል የጥሬ ዕቃ ግብዓቶች፤ የቧንቧ ዕቃዎች፤ የተለያዩ ለትምህርት እና ለንባብ አገልግሎት የሚውሉ መጽሐፎች ጨረታ ቁጥር (2) የሲቪል ሰራተኞች፤ የስፖርተኞች የሥራ ልብስና ጫማዎች እንዲሁም በህግ ታራሚዎች አገልግሎት የሚውል ዩኒፎርም ብትን ጨርቅ፤ የእንስሳት መኖ ግብዓቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው ድርጅት ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት፡-

  1. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልግ ሁሉ፤ በሥራው መስክ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በዕቃ ግዢና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበት የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑ እና መለያ ቁጥር (Tin Number) ተመዝጋቢ የሆኑና የተሟላ ማስረጃ በ4 ኮፒ በማድረግ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች የተዘጋጀውን አንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመሰስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ለእያንዳንዱ ሰነድ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 100000797188 አ/አ ማረሚያ ቤት እደጥበባት ማዕከል በሚል ገንዘቡን ገቢ በማድረግ ከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ማዕከል ግዥ ክንውን ቡድን 2 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 2 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡ ማ/ቤቱ የሚገዛቸውን ዕቃዎች ዝርዝር በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ተዘርዝሮ ቀርቧል፡፡
  3. ተጫራቾች ከላይ በጨረታ ቁጥር 1-2 ለተጠቀሱት ጨረታዎች የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚመለስ ለእያንዳንዳቸው ብር 50,000.00 (ሀምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረለት ሲ.ፒ.ኦ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች አንዱ በሌላው ተጫራች ሰነድ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት የለውም፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ናሙና እንዲያቀርብ የተጠየቀባቸው ናሙናውን በጨረታ መክፈቻ ቀን ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሠነድ መግዛትና የመተዳደሪያ ሃሳባቸውን በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ አሽገው በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፣
  6. ተጫራቾች የጨረታ ቁጥር 1 መስከረም 26/2019ዓ/ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዳቸውን ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በዕለቱ በ4፡15 ሰዓት በማረ/ቤቱ በግዥ ክንውን ቢሮ ይከፈታል፡፡
  7. የጨረታ ቁጥር 2 መስከረም 27/2019ዓ/ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታውን ሰነድ ማስገባት ይችላሉ፡፡ በዕለቱ በ4፡15 ሰዓት በማ/ቤቱ አደራሽ ይከፈታል፡፡
  8. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ማዕከል ገላን በሚገኘው ዕቃ ግ/ቤት አምጥተው ያስረክባሉ፡፡
  9. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ሳይለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
  10. ማረሚያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ተጫራቾች ፕሮፎርማቸው ላይ ዋጋ ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ የሌለበት ጎላ ብሎ የሚነበብ ፅሑፍ መሆን ይገባዋል፤ ስርዝ ድልዝ ያለበት ዋጋ ተቀባይነት የለውም፡፡ በአሃዝና በፈደል መፃፍ ይጠበቅባቸዋል፡፡

አድራሻ፦ የከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ማዕከል ገላን

የከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ማዕከል

✨ messages.ai_summary
Ethiopia's High Security Prison Center seeks suppliers for Lot 1: wood/metal raw materials, pipes, and educational books; Lot 2: civil servant and athlete workwear, shoes, inmate uniforms, fabric, and animal feed. Bidders need a valid trade license, tax clearance, VAT and TIN registration, and must submit samples.
Save Tender