Tender Detail

Tender Details

  • Company የአዳማ ከተማ አስተዳደር
  • Address አዳማ ፣ኦሮሚያ, Phone: 0938709102
  • Website
  • Deadline13 Oct 2026, 5:30 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) የማይመለስ
  • Bid Securityየጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ መጠን አልተገለጸም።
  • opening dateጨረታው አየር ላይ ለተከታታይ 21 ቀን ቆይቶ በ 21 ኛው ቀን 4፡300 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  • Categories Building Construction , Land , House, Building And Warehouse , Sales, Disposals And Foreclosure

የአዳማ ከተማ አስተዳደር በከተማ አስተዳደሩ በመኖሪያ ቤቶች ላይ የሚስተዋለውን የፍላጎትና የአቅርቦት አለመጣጣም ችግር ለመፍታት በግልፅ ጨረታ መግዛት ለሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብ ወይም የግል ወይም የመንግስት ድርጅት ወይም አክሲዮን ማህበር አወዳድሮ በሸያጭ ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡

የአዳማ ከተማ አስተዳደር


የጨረታ ማስታወቂያ

የአዳማ ከተማ አስተዳደር በከተማ አስተዳደሩ በመኖሪያ ቤቶች ላይ የሚስተዋለውን የፍላጎትና የአቅርቦት አለመጣጣም ችግር ለመፍታት ወጪ ቆጣቢ ቤቶችን ገንብቶ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ እንዲችል በመንግስት በተመደበ ካፒታል በጀት በቦሌ ከፍለ ከተማ አንዶዴ ወረዳ ተገንብተው የተጠናቀቁ ባለ 5 ወለል በቂ የመኪና ማቆሚያ የ24 ሰዓት የውሃ እና መብራት አገልግሎት፣ ለተለያዩ ዝግጅቶች የሚሆን የጋራ ቦታ፣ በቂ የልጆች መጫወቻ ቦታ እና የጋራ መናፈሻ ቦታ ያላቸው ባለ አንድ መኝታ፣ ባለ ሁለት መኝታ እና እስቱዲዮ 539 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ባሉበት ሁኔታ በካሬ የመነሻ ዋጋ በግልፅ ጨረታ መግዛት ለሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብ ወይም የግል ወይም የመንግስት ድርጅት ወይም አክሲዮን ማህበር አወዳድሮ በሸያጭ ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ማንኛውም ለጨረታ የቀረቡ የመኖሪያ ቤቶችን ለመግዛት የሚፈልግ ዜግነቱ ኢትዮጵያዊ የሆነ ግለሰብ፣ የግል ድርጅት ወይም ለሰራተኞቻቸው መግዛት የሚፈልጉ የመንግስት ወይም የግል ወይም አክሲዮን ማህበራት ወይም ድርጅቶች ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 1:30 ድረስ በመቅረብ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በስንቄ ባንክ የአካውንት ቁጥር 1054558612 በመከፈል ፖስታ ቤት አከባቢ በሚገኘው ትልቁ ህንፃ በአዳማ ከተማ ገንዘብ/ፅ/ቤት ሶስተኛ ፎቅ ግዢ ክፍል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይቻላል፡፡

ጨረታው የሚከፈተው በ22 ኛው ቀን ከጥዋቱ 3፡00 ጀምሮ በተጫራቾች መመሪያ ላይ በተገለፀው ፕሮግራም መሰረት ይሆናል፣ የጨረታው መከፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ላይ የሚውል ከሆነ በተከታዩ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡ መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በ 0938-70-91-02 ይደውሉ

የአዳማ ከተማ አስተዳደር

✨ messages.ai_summary
Adama City Administration seeks to sell 539 completed condominium units (studio, one-, and two-bedroom) in Bole Sub-city, Andode District, to address housing demand-supply gaps. Open to Ethiopian individuals, private firms, or government/private/share companies buying for staff.
Save Tender