Tender Detail

Tender Details

  • Company የጥበብ እድገት ቅ/አ/አ/መ/ደ/ ት/ቤት
  • Address በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 04 ከወ/ሮ ቀለም ወርቅ መሰናዶ ት/ቤት ከፍብሎ ፊውቸር ሆፕስ ት/ቤት ፊት ለፊት 100 ሜትር ገባ ብሎ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0111 11 93 06
  • Website
  • Deadline01 Oct 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በአንድ ሎት
  • Bid Security15,000 (አስራ አምስት ሺ ብር) በባንክ የተረጋገጠ /CPO/
  • opening dateበዚያው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Categories Health Care, Medical Industry , Office Supplies And Services , Textile, Garment & Leather

በአራዳ ክ/ከ ወረዳ 04 የጥበብ እድገት ቅ/አ/አ/መ/ደ/ት/ቤትበመጀመሪያ ዙር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል፡፡

የጥበብ እድገት ቅ/አ/አ/መ/ደ/ ት/ቤት


የአንደኛ ዙር የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

በአራዳ ክ/ከ ወረዳ 04 የጥበብ እድገት ቅ/አ/አ/መ/ደ/ት/ቤት ሎት1፣ የደንብ ልብስ ግዥ፣ ሎት2 የደንብ ልብስ ስፌት፣ ሎት3 አላቂ የቢሮ እቃ እቃዎች፣ ሎት 4 አላቂ የህከምና እቃዎች፣ ሎት5 የትምህርት እቃዎች (የላብራቶሪ)፣ ሎት6 ሌሎች አላቂ እቃዎች የፅዳት እቃዎች ሎት7 ልዩ ልዩ መሳሪያዎች፣ ሎት8 ፕላንት ማሽነሪ እቃዎች፣ መሳሪያ እድሳት፣ ሎት(9) ፕላንት ማሽነሪ እና መሳሪያ መግዣ፣ ሎት10 ለህንፃ ቁሳቁስ እና ተገጣጣሚ መግዣዎች፣ ሎት11 ህትመት በመጀመሪያ ዙር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች ጨረታውን መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. የታደሰ ንግድ ፍቃድ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ በዘርፉ የተሰማሩበት መረጃ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑ እንድሁም በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፡፡
  2. ተጫራቾች በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት በት/ቤቱ ፋይናስ ቢሮ በመገኘት የማይመለስ ብር በአንድ ሎት 200 ብር (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመከፈል የግልፅ ጨረታ ሰነዱን በት/ቤቱ ፋይናስ እና ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር G+1/005 መግዛት ትችላላችሁ፡፡
  3. ተጫራቾች የሚጫረቱበት ዋጋ ስርዝ ድልዝ ሳይኖርበት ግልፅ በሆነ መንገድ ቫትን ጨምሮ በመሙላት ት/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡
  4. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  5. የጨረታ ማስከበሪያ 15,000 (አስራ አምስት ሺ ብር) ብቻ በባንክ የተረጋገጠ /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ት/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  7. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት እቃዎች ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ነገር ግን ቋሚ እቃ በፎቶ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  8. ተጫራቾች ዋጋ መሙላት ያለባቸው ት/ቤቱ ባዘጋጀው ሰነድ ብቻ ነው፡፡

አድራሻ፡- በአራዳ ክ/ከ ወረዳ 04 የጥበብ እድገት ቅ/አ/አ/መ/ደ/ት/ቤት ከወ/ሮ ቀለም ወርቅ መሰናዶ ት/ቤት ከፍ ብሎ ፊውቸር ሆፕስ ት/ቤት ፊት ለፊት 100 ሜትር ገባ ብሎ

ስተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 01111 - 19306/0913436612/0965684386

በአራዳ ክ/ከ ወረዳ 04 የጥበብ እድገት ቅ/አ/አ/መ/ደ/ት/ቤት

✨ messages.ai_summary
The school seeks suppliers for 11 lots: uniforms (purchase and sewing), consumable office, health, laboratory, cleaning and other supplies, various equipment, plant machinery (repair and purchase), building materials, and printing. Bidders must have a renewed license, tax and VAT registration, supplier listing, and submit samples or photos.
Save Tender