Tender Detail

Tender Details

  • Company የደ/ብርሃን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግል ማህበር
  • Address , Phone: 011 637 58 03
  • Website
  • Deadline06 Oct 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200 ብር
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateበዚሁ ዕለት 4፡30
  • Categories Wood And Wood Working , Disposal Sale

የደብረ ብርሃን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በፋብሪካው ግቢ በምርት ሂደት ላይ የሚመረቱ የተለያዩ ተረፈ ምርቶችን በተለያየ ክፍልፋይ (ሎት) ከፋፍሎ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

የደ/ብርሃን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግል ማህበር


ክፍል 1 ግልጽ የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

የደብረ ብርሃን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በፋብሪካው ግቢ በምርት ሂደት ላይ የሚመረቱ የተለያዩ ተረፈ ምርቶችን በተለያየ ክፍልፋይ (ሎት) ከፋፍሎ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ከዚህ በታች በቀረበው ዝርዝር መረጃ መሰረት መወዳደር የምትፈልጉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ የተረፈ ምርቶቹን አይነት እና ዝርዝር ስፔስፊኬሽን ከጨረታው መመሪያ ሰነድ ማግኘት ይቻላል ወይም በፋብሪካው ቦታ ላይ በአካል በመገኘት ማየት ይቻላል፤ የጨረታ ሰነዱን ከድርጅቱ ፋይናንስ ክፍል የማይመለስ 200 ብር ከፍሎ መግዛት ይቻላል፡፡

  1. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ሎት በጨረታው መመሪያ ላይ በተገለፀው የብር መጠን መሰረት በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ በሲፒኦ (CPO) ማስያዝ አለባቸው፡፡
  2. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ዋጋውን እና አስፈላጊ መረጃዎችን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በደ/ብርሃን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከጠዋቱ 02፡00 እስከ 11፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ16 ተከታታይ የካላንደር ቀናት አየር ላይ ይሆናል፤ ሆኖም ግን ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ዕለት 4፡30 ተጫራቾች ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፡፡
  4. የጨረታ መከፈቻው ቀን የበዓል ቀን ወይም እሁድ ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ወይም በማግስቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት 4፡30 ላይ ይከፈታል፡፡
  5. ተጫራቾቹ ከሥራ መስኩ ጋር ተያያዥነት ያለው ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤ የVAT እና TIN ሰርተፊኬት የማይመለስ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፤ በውክልና የሚወዳደሩ አካላት ከፍትህ ወይም ከሰነዶች ማረጋገጫ ህጋዊ የውክልና ሰነድ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. መሥሪያ ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

* ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0920322355 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

ደብረ ብርሃን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

✨ messages.ai_summary
Debre Birhan Wood Processing Association invites bids to buy various by-products generated during production at its factory, offered in separate lots. The tender document with types and specifications is available from the finance office or for on-site inspection. Bidders must submit a valid renewed business license, VAT and TIN certificates, and a CPO bid security per lot.
Not stated in the notice: bid security. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለተለያዩ አገልግሎት ሊውሉ የሚችሉ ንብረቶችን ባሉበት ቦታና ሁኔታ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ለመሸጥ እንደሚከተለው አቅርቧል፡፡

READ MORE