Tender Detail

Tender Details

  • Company በውሃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የኮምቦልቻ ዋና ማስተባበሪያ ጽ/ቤት
  • Address ኮምቦልቻ ከተማ ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0953281222
  • Website
  • Deadline09 Oct 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price1000.00(አንድ ሺ ብር)
  • Bid Securityየጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ መጠን በየሎቱ ይለያያል።
  • opening dateጨረታው አየር ላይ ለተከታታይ20 ቀን ቆይቶ በ20ኛው ቀን 8፡30 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  • Categories Machinery , Vehicle

ውኃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ዋናው መ/ቤት የኮርፖሬሽኑን ሥራ ለማፋጠን ለተለያዩ ለፕሮጀከቶች አገልግሎት የሚሆን የተለያዩ ማሽነሪዎችና ተሽከርካሪዎች የኪራይ የአገልግሎት ግዥ ህጋዊ ከሆኑ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በውሃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የኮምቦልቻ ዋና ማስተባበሪያ ጽ/ቤት


ሃገር አቀፍ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 የጨረታ ቁጥር WWC 02/2019

ውኃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ዋናው መ/ቤት የኮርፖሬሽኑን ሥራ ለማፋጠን ለተለያዩ ለፕሮጀከቶች አገልግሎት የሚሆን የተለያዩ ማሽነሪዎችና ተሽከርካሪዎች የኪራይ የአገልግሎት ግዥ ህጋዊ ከሆኑ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ አቅራቢዎች የሚከተሉትን ህጋዊ ሁኔታዎች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ፡፡

1- የዘመኑን ግብር ከፍለው በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ፤የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ፤የቫት ምዝገባ የምስክርወረቀት የንግድ የምዝገባ ምስክር ወረቀት እና የንብረቱ ባለቤት ስለመሆኑ ማስረጃ ያላቸው መሆን አለበት፡፡ ተጫራቾች እነዚህንና ሌሎች ተያያዥነት ያላቸውን መረጃዎች ኮፒ በማድረግ በጀርባዉ ፊርማና ማህተም በማድረግ በመጫረቻ ሰነዶቻቸው ላይ ማካተት ይጠበቅባቸዋል፡፡

2- የጨረታ አሸናፊ የሚወሰነው በጨረታ ሰነዱ በተመለከቱት መስፈርቶች መሠረት ይሆናል፡፡

3- በዚህ ጨረታ መሳተፍ የምትፈልጉ ድርጅቶች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ 20 /ሃያ/ተከታታይ ቀናት ውስጥ በመምጣት የማይመለስ ብር 1000.00 /አንድ ሺ ብር/ በቀጥታ ከኮርፖሬሽናችን የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡ ሰነዱ የሚሸጥባቸው ቦታዎች ባህር ዳር ዋናው ቢሮ በአዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት እና ኮምቦልቻ ውኃ ሥራዎች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ይገኛል፡፡

4- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የመሣሪያ ብዛት መጠን የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ቀላል ተሽከርካሪ /አምቡላንስ ፣ዳብል ጋቢና፣ ሲንግልጋቢና፣ ሚኒ ጋቢና፣ ሚኒባስ፣ አውቶሞቢል፣ ስቴሽንዋግንና ተመሳሳይ ለሆኑት /20 ሺህ ብር/፣ መለስተኛ የህዝብና የጭነት ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች /አይሱዙና አውቶብስ/ 25ሺህ ብር፣ ከባድ ተሽከርካሪ /ገልባጭ 120 ኩንታል በላይ የሚጭኑ የደረቅ እና የፈሳሽ ጭነት ማጓጓዣ ፣ ሚክሰር፣ ትራከተር፣ ከሬን/ 30 ሺህ ብር፣ ለቀላል ማሸነሪዎች /ኮምፖክተር፣ ሎደር/ 35 ሺህ ብር እና ለከባድ ማሽነሪነዎች /ዶዘር፣ ኤከስካቫተር፣ ግሬደር፣ ሎቤድ/ 40 ሺህ ብር በባንከ በተረጋገጠ ሰነድ /CPO/ ወይም ያለቅድመ ሁኔታ እንደተጠየቀ የሚከፈል /Unconditional Bank guarantee/ የባንክጋራንቲ በማሰራት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

5- ተጫራቾች የማወዳደሪያ ሠነዳቸው በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 20 ቀናት ውስጥ የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ባህር ዳር ከተማ ከሚገኘው ዋናው መስሪያ ቤታችን ውሃ ስራዎች ኮርፖሬሽን ሶስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 25 በመቅረብ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡

6- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ20ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን 8፡30 መሰናዶ ት/ቤት ጐን በሚገኘው የኮርፖሬሽኑ ህንጻ 3ኛ ፎቅ የግዥ አፊሰሮች ቢሮ ቁጥር 25 ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች በራሳቸው ፈቃድ ጨረታው በሚከፈትበት ወቅት ባይገኙም ጨረታውን ለመከፈት አያስተጓጉሉም፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በጨረታ ሂደቱ ለሚተላለፉ ውሳኔዎች ተገዥ ይሆናሉ፡፡ የጨረታው መከፈቻ እና መዝጊያ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው የሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል፡፡

7- ተጫራቾች በጨረታው ካሸነፉ በኮርፖሬሽኑ ስምምነት መሰረት የቅድመ ክፍያ ሊከፍል ይችላል፡፡

8- ተጫራቾች በጨረታው መመሪያ መሠረት የመጫረቻ ሰነዳቸውን ማቅረብ አለባቸው ከጨረታው መመሪያ ውጭየሚቀርብ ማንኛውም ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡

9- ተጫራቾች በአንድ ማሸን ወይም ተሽከርካሪ መወዳደር የሚችሉት አንድ ኘሮጀከት ብቻ ላይ ነው፡፡

10- ኮርፖሬሽን የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

11- ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፡፡

የስልክ ቁጥር ባህር ዳር  058-222-1479 ወይም 058-226-5203

አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት 011-443-2595

ኮምቦልቻ ምስራቅ አማራ ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት 033-551-0230 ወይም  033-551-0848

ውሃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን

✨ messages.ai_summary
Water Works Corporation seeks legal entities to rent out various machinery and vehicles for its projects through open national tender. Bidders must have a valid business license, TIN, VAT registration, and proof of asset ownership. One project per machine/vehicle. The Corporation may cancel the tender in whole or in part.
Save Tender

የWindows of Hope 2026 ፕሮጀክት ያሰባሰባቸው አስር አጋር ድርጅቶች ለቆዳ እና የልብስ ስፌት ስራ ማሽኖች አቅርቦት ብቁ የሆኑ አቅራቢዎችን በድጋሚ...

READ MORE
Procurement of Machinery

READ MORE