Tender Detail

Tender Details


በጉለሌ/ከ/ከተማ ወረዳ 05 የጀኔራል ታደሰ ብሩ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ 2019 ለመደበኛ በጀትና የዉስጥ ገቢ በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል ሎት 1. የጽሕፈት እና የትምህርት መሳሪያዎች፣ ሎት 2. አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ ሎት 3. አላቂ የጽዳት ዕቃዎች፣ ሎት 4. የደንብ ልብስ ፣ ሎት 5. የደንብ ልብስ ስፌት ፣ ሎት 6. ቋሚ የፈርኒቸር ዕቃዎች ፣ ሎት7. ቋሚ የኤሌከትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ሎት 8

በጉለሌ ክ/ከተማ ት/ት ጽ/ቤት የጄኔራል ታደሰ ብሩ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ 001/2019

በጉለሌ/ከ/ከተማ ወረዳ 05 የጀኔራል ታደሰ ብሩ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ 2019 ለመደበኛ በጀትና የዉስጥ ገቢ በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል ሎት 1. የጽሕፈት እና የትምህርት መሳሪያዎች፣ ሎት 2. አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ ሎት 3. አላቂ የጽዳት ዕቃዎች፣ ሎት 4. የደንብ ልብስ ፣ ሎት 5. የደንብ ልብስ ስፌት ፣ ሎት 6. ቋሚ የፈርኒቸር ዕቃዎች ፣ ሎት7. ቋሚ የኤሌከትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ሎት 8 የሕንፃ መሳሪያ ዕቃዎች ፣ ሎት 9. ህትመት ፣ ሎት 10. የኤሌክትሮኒከስ ጥገና ፣ሎት 11. የጭነት መኪና ኪራይ አግልግሎት እና ሎት 12. የካፌ አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ስለሚፈልግ ተጫራቾች ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርት ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡ ተጫራቾች ይህንኑ የሚገልፅ ማስረጃ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

2. ተወዳዳሪዎች በግብር ዓመቱ ተገቢውን የታክስ እና ግብር ግዴታ የተወጡ መሆኑን የሚያሳይ የታከስ ከሊራንስ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

3.እንዳስፈላጊነቱ የብቃት ማረጋገጫ ሰነዶች፣ ከአምራች ወይም ከአከፋፋዮች የሚሰጥ ውክልና ወይም የእሽሙር ማህበር መመስረቻ ሰነድ እንዲሁም ሌሎችም አስፈላጊ ሰነዶች ተካተው መቅረብ አለበት፡፡

4.ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በጉለሌ/ከ/ከተማ ወረዳ 05 ከዊንጌት ወደ አስኮ በሚወሰደው መንገድ ካዎ ጄጄ የምግብ ማምረቻ ኮምፕሌከስ ቀጥሎ በሚገኘው ጄኔራል ታደሰ ብሩ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት አዲሱ ህንፃ ቢሮ ቁጥር 6 የማይመለስ በየሎቱ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመከፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ በተጨማሪም ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝ ኮፒ ከሰነዱ ጋር አያይዘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው ፡፡

5. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዕቃ ጥራት ያለው ደረጃውን የጠበቀ ስለመሆኑ ናሙና ማቅረብ ባለባቸው ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

6.ተጫራቾች የዕቃዎች ዝርዝር እና የጨረታ ማወዳደሪያ ሰነድ ላይ ስማችሁን በመፃፍ ፊርማችሁንና አድራሻችሁን ማስፈርና እንደ ሚታይ አርጋችሁ ማህተም በማድረግ ማስታወቂያ ከወጣ ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት በጉለሌ/ከ/ከተማ ወረዳ 05 ከዊንጌት ወደ አስኮ በሚወሰደው መንገድ ካዎ ጄጄ የምግብ ማምረቻ ኮምፕሌክስ ቀጥሎ በሚገኘው ጄኔራል ታደሰ ብሩ አጠቃላይ2ኛ ደረጃ ት/ቤት አዲሱ ህንፃ ቢሮ ቁጥር 106 ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ስታስገቡ ከሙሉ ፋይል ኦርጅናል እና ኮፒ ሰነድ ጋር እስከ 10 ኛው ቀን 11:00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያው በወጣበት በከኛው ቀን በ 4፡30 በጀኔራል ታደሰ ብሩ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ይከፈታል፡፡ የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እና አሁድ ወይም በበዓል ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተገለፀው ሰዓት ይከፈታል፡፡

8. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች በሰነድ የሰጡት ዋጋ መለወጥ ማሻሻል ወይም ከውድድሩ እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡

9. የማወዳደሪያ ዋጋ ከቫት ጋር መሞላት አለበት፡፡

10. ተጫራቾች የጨረታው ማስከበሪያ ለሎት 1. ብር 6,000 (ስድስት ሺህ ብር ብቻ) ለሎት 2. ብር14,500 (አስራ አራት ሺህ አምስት መቶ ብር ብቻ) ለሎት 3. ብር 4,000 (አራት ሺህ ብር ብቻ) ለሎት 4. ብር 14,000 (አስራ አራት ሺህ ብር ብቻ) ለሎት 5. ብር 2,000 (ሁለት ሺህ ብር ብቻ) ለሎት 6. ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር ብቻ) ለሎት 7. ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር ብቻ) ለሎት 8. ብር 3.000 (ሶስት ሺህ ብር ብቻ) ለሎት 9. ብር 3.000(ሶስት ሺህ ብር ብቻ)ለሎት 10. ብር 1,000(አንድ ሺህ ብር ብቻ)ለሎት 11 ብር 1000 (አንድ ሺህ ብር ብቻ) ለሎት 12 ብር 9,500 (ዘጠኝ ሺህ አምስት መቶ ብር ብቻ) በባንክ በተመሰከረለት CPO ማስያዝ ይኖርባችኋል፡፡

10. ት/ቤቱ እንደ አስፈላጊነቱ የዕቃውን ብዛት ከውል በፊት 20% መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል፡፡

11. አሸናፊው ድርጅት ዕቃዎቹን እስከ ጀኔራል ታደሰ ብሩ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ንብረት ክፍል ድርስ በራሱ ትራንስፖርት አጠቃሎ ማስገባት አለበት፡፡

12. በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጃችሁ መወዳደር የምትችሉት ባመረታችሁት ምርት ወይም እሴት በጨመራችሁት ብቻ ሲሆን ከዚህ ውጪ ግን እንደ ማንኛውም እጩ ተወዳዳሪ የጨረታ ሰነድ መግዛትና የውል ማስከበሪያ ሲፒኦ (CPO) በማስያዝ መወዳደር የምትችሉ ይሆናል፡፡

13. ት/ቤቱ እንደአስፈላጊነቱ የጠቅላላ ዋጋውን 25 % በተጨማሪ ትዕዛዝ በመስጠት ካሽ መፈፀም ይችላል፡፡

14. ሰነዱ ላይ ድልዝ ስርዝ መኖር የለበትም ካለበት ውድቅ ይሆናል፡፡

15  መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር +251112804292,0989066757

አድራሻ፦ በጉለሌ/ከ/ከተማ ወረዳ 05 ከዊንጌት ወደ አስኮ በሚወሰደው መንገድ ካዎ ጄጄ የምግብ ማምረቻ ኮምፕሌከስ ቀጥሎ በሚገኘው ጄኔራል ታደሰ ብሩ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት አዲሱ ህንፃ

 

በጉለሌ/ክ/ከተማ ወረዳ 05 የጀኔራስ ታደሰ ብሩ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት

✨ messages.ai_summary
General Tadesse Biru Secondary School seeks suppliers for 12 lots: stationery and educational materials, consumable office and cleaning supplies, uniforms and tailoring, furniture, electronics and repairs, building materials, printing, truck rental, and cafeteria services. Bidders need a valid trade license, tax registration, clearance, samples, and manufacturer or supplier authorization.
Save Tender