ገነት ሆቴል በግቢው ውስጥ ያሉትን ነባር የመጸዳጃ እና መታጠቢያ ክፍሎች የግንባታ እድሳት ስራን ለማሰራት ብቁ የሆኑ የሀገር በቀል የህንጻ ወይም የጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ደረጃ 5(አምስት) እና ከዚያ በላይ የሆኑ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ በማወዳደር ማሰራት ይፈልጋል።
ገነት ሆቴል
ለ2ኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ የነባር መጸዳጃ እና መታጠቢያ ክፍሎች የአድሳት ስራ
ገነት ሆቴል በግቢው ውስጥ ያሉትን ነባር የመጸዳጃ እና መታጠቢያ ክፍሎች የግንባታ እድሳት ስራን ለማሰራት ብቁ የሆኑ የሀገር በቀል የህንጻ ወይም የጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ደረጃ 5(አምስት) እና ከዚያ በላይ የሆኑ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ በማወዳደር ማሰራት ይፈልጋል። ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች እንዲሁም የሰው ኃይል፣ ማሽን እና የግንባታ ግብዓቶችን ማሟላት የሚችሉ ስራ ተቋራጮች ስራውን ለማከናወን በግልፅ ጨረታ ውድድር መሳተፍ ይችላሉ።
- በህንጻ ወይም በጠቅላላ ስራ ተቋራጭነት ደረጃ -5(አምስት) እና ከዚያ በላይ ሆነው የታደሰ ፍቃድ ያላቸው።
- የ2018/19 ዓ.ም ዘመን የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት(VAT) ያላቸው።
- የግብር ከፋይ ምዝገባና ሰርተፍኬትና መለያ ቁጥር (TIN) ሰነድ ያላቸው።
- በጨረታ ለመወዳደር የሚያስችል የታደሰ የታክስ ክሊራንስ ፍቃድ ያላቸው።
- ተጫራቾች ስለጨረታው ሙሉ ዝርዝር ሁኔታ የያዘውን የጨረታ ሰነድ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ታሳቢ የሚደርግ 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ጊዜ ውስጥ ከድርጅታችን የፋይናንስ ቢሮ ክፍል የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 500.00 (አምስት መቶ ብር) ከፍለው መውሰድ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 80,000.00 (ሰማንያ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና "ለገነት ሆቴል" በሚል በማሰራት ከቴክኒካል ሰነድ ጋር ለብቻው በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የቴክኒካል ሰነድ እና ፋይናንሻል ሰነድ ለእያንዳንዳቸው አንድ ኮፒ በማዘጋጀት በተናጥል ለየብቻ በማሸግ በጥቅል በአንድ በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ እስከ አስራ አምስተኛው (15) ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ድረስ በድርጅቱ የፋይናንስ ክፍል ቢሮ ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፤ አስራ አምስተኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ የጨረታው መክፈቻ ቀጣይ ባለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ተወካዮች ባሉበት በአስራ አምስተኛ (15) ከቀኑ 9፡00 በድርጅቱ አዳራሽ ይከፈታል።
- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- አ/አ ከሜክሲኮ ወደ ቄራ በሚወስደው መንገድ ካሳ ግራንድ ሞል ፊት ለፊት
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- 0115-504701/0911-250641/0939-500000
ገነት ሆቴል
✨ messages.ai_summary
Genet Hotel invites eligible local building or general works contractors (Grade 5 and above) to renovate its existing toilet and bathroom facilities. Bidders must meet requirements including valid licenses, VAT registration, TIN, and tax clearance, and demonstrate capacity in manpower, machinery, and construction inputs.
