የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ግብርና ቢሮ ለግብርና ኖራ የማዳበሪያ ከረጢት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ግብርና ቢሮ
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 011/18
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ግብርና ቢሮ ለግብርና ኖራ የማዳበሪያ ከረጢት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
| ተ.ቁ | የዕቃው ዓይነት | መለኪያ | ብዛት | የጨረታ ማስከበሪያ | የሚታሸግበት ሰዓት | የሚከፈትበት ሰዓት |
| 1 | ለግብርና ኖራ የማዳበሪያ ከረጢት | በቁጥር | 25.000 | 20,000 | 9:00 ሰዓት | 9:10 ሰዓት |
መሟላት ያለባቸው ገደቦች
- በስራ ዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ፣ ታክስ ክሊራንስ፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ለ45 ቀናት የፀና መሆን ይኖርበታል።
- በተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና፣ ጥሬ ገንዘብ ያስያዙበት ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች በቢሮው የተዘጋጀውን መደበኛ የጨረታ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን 8/01/2019 ዓ/ም እስከ 9፡00 ሰዓት የማይመለስ ብር 200 ለሰነድ በመከፈል ዱራሜ ከተማ በሚገኘው የግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 003 መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ (ፕሮፎርማ) በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 22/1/2019 ዓ/ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ የቴክኒካልና ፋይናንሻል የመጫረቻ ሠነዶችን በአንድ ፖስታ በማዘጋጀት በቢሮው የግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 003 ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
- የጨረታው ሳጥን በቀን 22/1/2019 ዓ/ም በቀኑ 9:10 ሰዓት ተጫራቾች ተወካዮቻቸው በተገኙበት በቢሮው የግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 003 ይከፈታል።
- ቢሮው ለዚህ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ግብርና ቢሮ
✨ messages.ai_summary
The Central Ethiopia Regional State Agriculture Bureau seeks to buy fertilizer bags for agricultural lime via open tender. Bidders must submit a renewed business license, commercial registration, TIN, VAT, tax clearance, and supplier registration certificate; prices must remain valid for 45 days.
