Tender Detail

Tender Details

  • Company የድሬዳዋ አስተዳደር የሳቢያን ጠቅላላ ሆስፒታል ድሬዳዋ
  • Address ድሬዳዋ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0251124968
  • Website
  • Deadline26 Sep 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceየማይመለስ ብር 500
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateበዚያኑ ቀን ከጠዋቱ 4፡30
  • Categories Steel, Metals And Aluminium , Disposal Sale , Used Items

በድሬደዋ አስተዳደር ሳቢያን ጠቅላላ ሆስፒታል ቅጥር ግቢ በሰንጠረገዝ የተመለከቱትን አዳዲስና ያገለገሉ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ተጫራቾችን ይጋብዛል።

የድሬዳዋ አስተዳደር የሳቢያን ጠቅላላ ሆስፒታል ድሬዳዋ


የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

በድሬደዋ አስተዳደር ሳቢያን ጠቅላላ ሆስፒታል ቅጥር ግቢ በሰንጠረገዝ የተመለከቱትን አዳዲስና ያገለገሉ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ተጫራቾችን ይጋብዛል።

ተ.ቁ የብረት ዓይነት መለኪያ ብዛት የእቃዎቹ ሁኔታና የሚገኙበት ቦታ
1 ልዩ ልዩ ያገለገሉ ብረትና የብረት ዕቃዎችና ሌሎች ቁርጥራጭ ብረት (Scrap metal) ኪ.ግ ተመዝኖ  
2 የተለያዩ ጎማዎች በቁጥር    
3 ልዩ ልዩ ያገለገሉ እንጨትና የእንጨት ዕቃዎችና ሌሎች ቁርጥራጭ እንጨቶች ኪ.ግ ተመዝኖ  

ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡-

  1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት (አምስት መቶ ብር) A15 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 500 በመክፈል በሳቢያን ጠቅላላ ሆስፒታል ግዢ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቁጥር 3 በመቅረብ የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
  2. ተጫራቾች ሰነድ ገዝተው ለሽያጭ የተዘጋጁትን ንብረቶች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ከ3፡00 እስከ 1፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ በሳቢያን ጠቅላላ ሆስፒታል ግቢ በመገኘት መመልከት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ንብረት ለጨረታ ማስከበሪያ በጨረታ ሰነዱ ውስጥ የተገለፀውን የብር መጠን በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በሳቢያን ጠቅላላ ሆስፒታል ስም አሰርተው ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ሣጥኑ ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረት በመምረጥ የሚገዙበትን ዋጋ በአኃዝና በፊደል ለይተው ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው ጽፈው ከፈረሙ በኋላ በኤንቬሎፕ አሽገው ሳቢያን ጠቅላላ ሆስፒታል ግ/ን/ፋ አዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 03 በመምጣት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ የስራ ቀናት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው፡፡
  5. የጨረታ ሰነዱ የሚከፈትበት ቀን ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 የስራ ቀናት ከቆየ በኋላ በ16ኛው ቀን ጠዋት በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሳቢያን ጠቅላላ ሆስፒታል ግ/ን/ፋ/ ኢ/ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 03 ውስጥ ይከፈታል፡፡
  6. ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ተካፋይ ሆኖ ጨረታው ከተዘጋ በኋላ ከጨረታው መውጣት ወይም የሰጠውን ዋጋ መለወጥ ወይም ማሻሻል አይችልም፡፡
  7. የጨረታ መገምገሚያ መስፈርት ከፍተኛ ዋጋ እና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ናቸው፡፡
  8. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው ከ7 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል፡፡
  9. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ዕቃውን በ10 ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው፡፡
  10. ሆስፒታሉ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ እና ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 025124968 / 0912058798 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡ ወይም ሳቢያን ጠቅላላ ሆስፒታል ግዢ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 03 በመምጣት ተገቢውን መረጃ ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የድሬደዋ አስተዳደር የሳቢያን ጠቅላላ ሆስፒታል

✨ messages.ai_summary
Sabiyan General Hospital invites bidders to buy used and new items via open auction: scrap metal, various tires, and used wood/wood items. Bidders must buy the tender document, inspect items on site, submit a CPO bid security, and pay the full winning price within the set period.
Not stated in the notice: bid security. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender