Tender Detail

Tender Details

  • Company በኮልፌ ቀራንዮ ክፍስ ከተማ በወረዳ 11 ረጲ ጃፓን ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
  • Address Addis Ababa Ethiopia, Phone: ------
  • Website
  • Deadline28 Sep 2026, 10:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceበሎት 100 /መቶ ብር ብቻ/
  • Bid Securityለሎት 1፣ ለሎት 2፣ ለሎት 3 ለሎት 4፣ ለሎት 5 ለአምስቱም ሎቶች 15,000.00 /አስራ አምስት ሺህ ብር ብቻ/ እና ለሎት 6፣ ለሎት 7፣ ሎት 8 እና ሎት 9 ለአራቱም ሎቶች 10,000 /አስር ሺህ ብር/ /በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  • opening dateበ11ኛው ቀን 4፡30
  • Categories Office Supplies And Services , Textile, Garment & Leather , Medical Equipment And Supplies

በኮልፌ ቀራንዮ ከፍለ ከተማ በወረዳ 11 ውስጥ የረጲ ጃፓን ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2019 ዓ.ም የሥራ ዘመን በግልጽ ጨረታ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍስ ከተማ በወረዳ 11 ረጲ ጃፓን ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት


የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በኮልፌ ቀራንዮ ከፍለ ከተማ በወረዳ 11 ውስጥ የረጲ ጃፓን ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2019 ዓ.ም የሥራ ዘመን በግልጽ ጨረታ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት፡ ሎት 1 የቢሮ የተለያዩ የፅሕፈት መሣሪያ ዕቃዎች፣ ሎት 2 የደንብ ልብስ፣ ሎት 3 የሕክምና ዕቃ፣ ሎት 4 የላብራቶሪ ዕቃ፣ ሎት 5 የዕዳት ዕቃ፣ ሎት 6 ቋሚ ዕቃ፣ ሎት 7 የጥገና ዕቃ፣ ሎት 8 የኅትመት ሥራ ሎት 9 የውሃ መስመር ጥገና የኤሌክትሪክ መስመር ጥገና ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርት የሚያሟሉ ማንኛውም የዘርፉ ሕጋዊ ነጋዴዎች ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ ሕጋዊና የታደሰ ንግድ ፍቃድ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የሚያገኙበት ቦታ የረጲ ጃፓን ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቢሮ ቁጥር 3 የማይመለስ በሎት 100 /መቶ ብር ብቻ/ ከፍሎ መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሎት 1፣ ለሎት 2፣ ለሎት 3 ለሎት 4፣ ለሎት 5 ለአምስቱም ሎቶች 15,000.00 /አስራ አምስት ሺህ ብር ብቻ/ እና ለሎት 6፣ ለሎት 7፣ ሎት 8 እና ሎት 9 ለአራቱም ሎቶች 10,000 /አስር ሺህ ብር/ /በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቶች ናሙና የሚያስፈልጋቸዉ እቃዎች ጨረታ ከመክፈቱ 1 ቀን ቀደም ብሎ የድርጅቱን ሙሉ ስምና ሕጋዊ ማኅተም በማድረግ ቢሮ ቁጥር 3 ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ገገዢው እካል የሚገዛውን እቃ እስከ 20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
  6. በጨረታው አሸናፊ ድርጅት አሸናፊ መሆኑ ሲረጋገጥ ውል ለመዋዋል ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% ለውል ማስከበሪያ በሲፒኦ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  7. ተጫራቾች ለሚያቀርቧቸው እቃዎች ቴክኒካልና ፋይናንሻል ኦርጅናልና ኮፒ በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት እስከ 11፡30 ሰዓት ቆይቶ በዘኛው የሥራ ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  8. የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ 10 የሥራ ቀን እስከ 11፡30 ስዓት ቆይቶ በ11ኛ የሥራ ቀን 4፡00 ሰዓት ላይ የጨረታው ሳጥን ታሽጐ በ11ኛው ቀን 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  9. የእቃ ማጓጓዣ አሸናፊው ድርጅት ይሸፍናል፡፡
  10. ተጫራቾቹ የሚሞሉት ዋጋ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም ስርዝ ድልዝ ካለ ውድቅ ይሆናል።
  11. ተጫራቾቹ የሚያቀርቡት የአንዱ ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት፡፡ የአንዱን ዋጋ ቫትን ጨምሮ ካልተሞላ ውድቅ ይሆናል።
  12. ከጥቃቅንና አነስተኛ ተቋም የተደራጁ ከሆነ ከጥቃቅንና አነስተኛ አደራጅ ተቋም በኃላፊው የተፃፈ ወቅታዊ የሆነ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው፡፡ በባለሙያ የተፃፈ ከሆነ ተቀባይነት የለውም፡፡
  13. ይህ ጨረታ ከኛው ቀን ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ወደ ቀጣይ የሥራ ቀናት ይሻገራል፡፡
  14. ት/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡

አድራሻ፡ ካራ ቆሬ ወደ ወለቴ መሄጃ ረጲ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት አለፍ ብሎ በተለምዶ ጥላሁን ሜዳ የረጲ ጃፓን ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቢሮ ቁጥር 3

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0118-35-34-16 በመደወል ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍስ ከተማ በወረዳ 11 ረጲ ጃፓን ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት

✨ messages.ai_summary
The school seeks to procure assorted office supplies, uniforms, medical and laboratory items, printing, and water/electric line maintenance via open tender across nine lots. Eligible bidders must be licensed traders with renewed business licenses, TIN, and VAT registration. Samples may be required.
Save Tender