Tender Detail

Tender Details

  • Company የሣውላ ማረሚያ ተቋም የግዥ ፋ/ን/አስ/ር ደጋፊ ሥራ ሂደት
  • Address Southe Ethiopian REGIONAL state , Phone: ------
  • Website
  • Deadline26 Sep 2026, 10:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price300/ሦስት መቶ ብር/
  • Bid Security50,000.00/ሃምሳ ሺህ ብር/ብቻ በCPO የተረጋገጠ
  • opening dateዕለቱ በ4፡30
  • Categories Cleaning & Janitorial , Education And Training , Office Supplies And Services

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን በጎፋ ዞን የሣውላ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም በ2019 ዓ/ም የፅህፈት መሣሪያ፣ የፅዳት ዕቃ እና የትምህርት ቁሳቁስ አገልግሎት የሚውል፡- በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

የሣውላ ማረሚያ ተቋም የግዥ ፋ/ን/አስ/ር ደጋፊ ሥራ ሂደት


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን በጎፋ ዞን የሣውላ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም በ2019 ዓ/ም የፅህፈት መሣሪያ፣ የፅዳት ዕቃ እና የትምህርት ቁሳቁስ አገልግሎት የሚውል፡- በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች መስፈሪቱን የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

  1. በዘርፉ ንግድ ፍቃድ ያለው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈለ፡፡
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ የቫት ተመዝጋቢ የሆነ፡፡
  4. የግብር መለያ /Tin/ ቁጥር ያለው፡፡
  5. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  6. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በCPO የተረጋገጠ 50,000.00/ሃምሳ ሺህ ብር/ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች ከ1 እስከ 5 የተጠቀሰውን ማስረጃዎችን እና የማጫረቻ ሠነድ አርጅናልና ኮፕ በተለያዩ ፖስታ ውስጥ በማስገባት በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በመንግስት የሥራ ሰዓት ማስገባት አለባቸው፡፡
  8. የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በመንግስት የሥራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 9 በመቅረብ የማይመለስ 300/ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሠነድ መግዛት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  9. ተጫራቾች ዕቃውን በራሳቸው ወጪ እስከ ሣውላ ማረሚያ ተቋም ግቢ አምጥተው ማስረከብ አለባቸው፡፡
  10. የጨረታው አሸናፊ ሆነው የተገኙ ተጫራች የዕቃዎችን አጠቃላይ ዋጋ በ10% በባንክ የተረጋገጠ ቼክ ወይም /Cpo/ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከሣውላ ማረሚያ ተቋም ግዥ ፋ/ን/አስ/ር ደጋፊ ሥራ ሂደት ጋር የውል ስምምነት መፈፀም ይጠበቅባቸዋል፡፡
  11. ተጫራቾች ጨረታው በሚከፈትበት ቀን ከሁሉም ዓይነት ናሙና ይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡
  12. የጨረታ ማስታወቂያ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ለ15 ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሳጥን በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ዕለቱ በ4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡ ዕለቱ ቅዳሜ እሁድ እና በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በመንግስት ሥራ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  13. በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ መወዳደር ተቀባይነት የለውም፡፡
  14. ማረሚያ ተቋሙ የተሻለ አማራጭ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0916479909/0916877379

የሣውላ ማረሚያ ተቋም የግዥ ፋ/ን/አስ/ር ደጋፊ ሥራ ሂደት

✨ messages.ai_summary
Sawla Prison Police Institution seeks to purchase office supplies, cleaning materials, and educational materials via open tender. Bidders must hold a valid trade license, be VAT-registered with a TIN, provide a supplier registration certificate, and submit samples on the bid opening day.
Save Tender