Tender Detail

Tender Details

  • Company ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዴቨሎፕመንት /ECD/
  • Address Addis Ababa, Ethiopia, Phone: 098288 2826
  • Website
  • Deadline25 Sep 2026, 5:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceየጨረታ ሰነድ መግዣ ብር መጠን አልተገለጸም ።
  • Bid Securityየጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ መጠን በየሎቱ ይለያያል።
  • opening dateየጨረታውን መክፈቻ ቀን አልተገለጸም ፡፡
  • Categories Health Care, Medical Industry Materials And Machinery

ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዴቨሎፕመንት / ECD/ እና ፔስታሎዚ የህፃናት መርጃ ድርጅት /PCF/ በጋራ በመሆን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥር በሚገኙ 16 የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ "በ16 የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተማሪዎችን ውጤት ማሻሻል " የሚል ሙሉ ትኩረቱን በትምህርት ጥራት ላይ ያደረገ ፕሮጀከት በተግበር ላይ ይገኛሉ።

ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዴቨሎፕመንት /ECD/


የጨረታ ማስታወቂያ

ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዴቨሎፕመንት / ECD/ እና ፔስታሎዚ የህፃናት መርጃ ድርጅት /PCF/ በጋራ በመሆን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥር በሚገኙ 16 የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ "በ16 የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተማሪዎችን ውጤት ማሻሻል " የሚል ሙሉ ትኩረቱን በትምህርት ጥራት ላይ ያደረገ ፕሮጀከት በተግበር ላይ ይገኛሉ። በመሆኑም ድርጅታችን ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዴቨሎፕመንት / ECD/ ለነዚህ አጋርትምህርት ቤቶች ለክበባት ድጋፍ እና ለተለያዩ የትምህርት ቤት አገልግሎቶች የሚውሉ ግብዓቶችን ለመግዛት አቅዷል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉትን ቁሳቁሶች ለማቅረብ የምትፈልጉ እና መስፈርቶቹን የምታሟሉ አቅራቢዎች በጨረታው መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ የሚገዙት ቁሳቁሶችም የሚከተሉት ናቸው፡፡

ሎት ዘርፍ ዝርዝር መረጃ ምርመራ
1 የከበባት ቁሳቁሶች ዝርዝር መረጃው በጨረታው ሰነድ ውስጥ ያገኙታል  
2 ለላቦራቶሪ፣ላይብረሪ እና ፣ ፔዳጎዲ ማዕከላት ዝርዝር መረጃው በጨረታው ሰነድ ውስጥ ያገኙታል  

ተጫራቾች ማሟላት ያስባቸው መስፈርቶች

1. ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣

2. የቲን ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፣

3. የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እና ሰርተፊኬቱን ማቅረብ የሚችሉ፣

4. ቁሳቁሶቹን በተቀመጠው ስፔሲፊኬሽን መሠረት ማቅረብ የሚችሉ፣

5. የእጅ በእጅ ሽያጭ ደረሰኝ የሚጠቀሙ ከሆነ በብርሃንና ሰላም የታተመ የኪው አር ኮድ ያለው ደረሰኝ የሚያቀርቡ

6. ያሸነፉበትን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት አጓጉዘው ድርጅቱ ወደሚያዘጋጀው ስቶር ማድረስ የሚችሉ፣ ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ ህጋዊ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከድርጅታችን የጨረታ ሰነዱን በነጻ በመውሰድ ቁሳቁሶቹን የምታቀርቡበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስገባትና መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡

አድራሻ፦ ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዲቨሎፕመንት /ECD/

አዲስ አበባ፣ ቦሴ አስም ህንፃ 7ኛ ፎቅ

ስልክ:- 0982 88 2826

ማሳሰቢያ

1. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ግብዓት ከማቅረባቸው በፊት ሳምፕል ማሳየት ይኖርባችኋል፡፡

2. ተጫራቾች የምታቀርቡት ዋጋ ሻትን ያካተተ መሆን አለመሆኑን በግልጽ ማሳየት ይኖርባችኋል፡፡ በትክክል ካልተገለጸ ቫት እንደተካተተ ተደረጎ ይቆጠራል፡፡

3. ድርጅታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ያለ ምንም ቅድመ ማስጠንቀቂያ እና ማስታወቂያ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዴቨሎፕመንት

✨ messages.ai_summary
Ethiopia Center for Development and Pestalozzi Children's Foundation seek suppliers for a project improving student performance in 16 Addis Ababa primary schools. Items: Lot 1 school club materials; Lot 2 laboratory, library and pedagogy center supplies. Bidders need a renewed business license, TIN, VAT registration, and must deliver to ECD's store.
Save Tender