የአብከመ ቤቶች ልማት ድርጅት ደሴ ቅ/ጽ/ቤት በደሴ ከተማ ለሚያስገነባው ለB+G+10 ህንጻ ዲዛይን የሚስራ ደረጃ ሁለት እና ከዚያ በላይ የሆነ አማካሪ ድርጅት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
አገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የአብከመ ቤቶች ልማት ድርጅት ደሴ ቅ/ጽ/ቤት በደሴ ከተማ ለሚያስገነባው ለB+G+10 ህንጻ ዲዛይን የሚስራ ደረጃ ሁለት እና ከዚያ በላይ የሆነ አማካሪ ድርጅት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች ማሟላት ለሚችሉ ተጫራቾች በሙሉ፡-
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፤
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች ከላይ 1-3 የተጠቀሱትን መረጃዎች የሚነበብ ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፤
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ላይ የሚሞሉት ዋጋ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት፤
- ተጫራቾች ለሞሉት የመወዳደሪያ ጠቅላላ ዋጋ መጠን 2% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ሲፒአ ወይንም በጥሬ ገንዘብ ከጨረታ ፖስታ ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው፤
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በጥንቃቄ በፖስታ አሽገው ስማቸውን፤ አድራሻቸውን፤ የድርጅቱን ማህተም እና ፊርማቸውን በእያንዳንዱ ዋጋ መሙያ ገፅ ላይ በማስቀመጥና ድርጅቱ የሚገኝበት ቢሮ ድረስ በመምጣት ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፤
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 1000.00 (አንድ ሽህ ብር) ብር ብቻ በመክፈል አብክመ ቤቶች ልማት ድርጅት ደሴ ቅ/ጽ/ቤት ግ/ክ ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 9 በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፤
- ተጫራቾች በሌላ ተወዳዳሪ ዋጋ ላይ ተንተርሰው መጫረት አይችሉም፤
- ማንኛውም ተጫራች በሰነዱ ላይ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ወይም በአካል በመቅረብ ማብራሪያ መጠየቅ ይችላል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 21 ተከታታይ የስራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ ቆይታ የሚኖረው ሲሆን በ21 ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ላይ የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ እለቱ ህዝባዊ በአል ወይም እሁድ ከሆነ በቀጣይ የስራ ቀን በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው ከተለየበት ቀን ጀምሮ ከ3 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 3 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ ብር 10 በመቶ በመከፈል /በማስያዝ ውል መያዝ ይኖርበታል ፡፡
- አሸናፊው የሚለው በTOR እና BID Document መሰረት ቴክኒካል ውጤቱ ከ70% በላይ የሆነ እና የተዘረዘሩትን ስራዎች ዝቅተኛ ዋጋ የሞላ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ አብክመ ቤቶች ልማት ድርጅት ደ/ቅ/ጽ/ቤት ሂደት ቢሮ ቁጥር 303 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር፡- 033 31217 27 ወይም 033 111 23 87 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
- ድርጅቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ እንዲሁም ተጫራቾች በጨረታ ማስታወቂያው ላይ ያልተገለፁ ሁኔታዎች ቢኖሩ በግዥ መመሪያው በኮንስትራክሽን ህጉ ተገዥ መሆን አለባቸው፡፡
ማሳሰቢያ፡- በዋጋ መሙያ ሰንጠረዥ ላይ ከተጠቀሰው ዝርዝር ስፔስፊኬሽን ውጭ በመሰረዝ እና በመደለዝ የራሱን ስፔስፊኬሽን የሞላ እና የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም የሌለበት ሰነድ የሚያቀርብ ተወዳዳሪ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
የአማራ ብሄራዊ ክልል መንግስት ቤቶች ልማት ድርጅት ደሴ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
