Tender Detail

Tender Details

  • Company በኦሮሚያ ክልል የምዕራብ ጉጂ ዞን ቀርጫ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
  • Address ኦሮሚያ ክልል፣ ኢትዮጵያ, Phone: 0936400183
  • Website
  • Deadline05 Sep 2026, 9:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር 1500
  • Bid Securityብር 10,000 (አስር ሺህ) ባንክ በተመሰከረለት ቼክ (CPO) ወይም በጥሬ ገንዘብ
  • opening dateበ3፡30 ሰዓት
  • Categories Furniture And Furnishing , Cleaning & Janitorial , Office Supplies And Services

በኦሮሚያ ክልል የምዕራብ ጉጂ ዞን ቀርጫ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በሥሩ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች ለ2019 በጀት አመት የሚያገለግሉ የተለያዩ የቢሮ ዕቃዎች

በኦሮሚያ ክልል የምዕራብ ጉጂ ዞን ቀርጫ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ክልል የምዕራብ ጉጂ ዞን ቀርጫ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በሥሩ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች ለ2019 በጀት አመት የሚያገለግሉ የተለያዩ የቢሮ ዕቃዎች

  1. የተለያዩ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች
  2. ፈርኒቸሮች
  3. ኤሌክትሮኒክስ
  4. የጽህፈት መሳሪያዎች
  5. የጽዳት መሳሪያዎች

በግልጽ ጨረታ አወዳደር መገዛት ይፈልጋል። ስለዚህ ከላይ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በዘርፍ የስራ ፍቃድ ያላቸው ተጫራቾች የሚከተሱትን መስፈርት ካሟሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. ተጫራቾች ህጋዊ የታደሰ የሥራ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ።
  2. ተጫራቾች ለተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 (አስራ አምስት) የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 1500 በመከፈል በቀርጫ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  4. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000 (አስር ሺህ) ባንክ በተመሰከረለት ቼክ (CPO) ወይም በጥሬ ገንዘብ ከኦርጅናል ጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለበት፡፡
  5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በግልጽ በመጻፍ ኮፒና ኦርጅናሉን በመለየት ለዚሁ ጨረታ የተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት።
  6. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የሚሆን ሲሆን በ11ኛው ቀን 3፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ3፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውና ታዛቢዎች በተገኙበት በቀርጫ ወረዳ ገንዘብ/ጽ/ቤት ይከፈታል።
  7. አሸናፊው አካል እንደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለተሸናፊ ወዲያውኑ ይመለሳል፡፡
  8. አሸናፊ በጨረታ መመሪያ መሰረት አሸናፊነቱ በጽሁፍ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ በ10/ቀን ውስጥ ለጨረታ ውል ማስከበሪያ የሚውል ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ በተመሰከረ ቼክ (CPO) ወይም ጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ከመስሪያ ቤቱ ጋር ውል መፈራረም አለበት። ይህ ባይፈጸም ቀደም ሲል ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
  9. ያሸነፉትን ዕቃዎች በራሱ ትራንስፖርት እስከ መ/ቤቱ ግምጃ ቤት ማምጣትና ፈርኒቸር ዕቃዎችን በራሱ ወጪ ማጋጣጠም የሚችል።
  10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ ሞባይል ቁጥር 0905873056/0918952198

በኦሮሚያ ክልል የምዕራብ ጉጂ ዞን ቀርጫ ከተማ ገንዘብ/ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Open tender for various office supplies for the 2019 budget year, including furniture, electronics, stationery, and cleaning equipment, for sector offices under Kercha Town Finance Office, West Guji Zone. Bidders must have a valid renewed license, paid current taxes, and VAT registration.
Save Tender