የሲ.ኤም.ሲ ሰንሻይን ቁ2 የመኖሪያ መንደር የጋራ ህንፃ ቤቶች ከብሎክ 49-114 የቤት ባለቤቶች ማህበር የአፓርትመንቱን መግቢያ በሮች፣ ቡዞች ፣የጥበቃ ቤቶች፣ የሽቦ አጥር እና የማስታወቂያ ቦርድ በጥራት እና በተገቢው የቴክኒክ መስፈርት ብቁ በሆኑ ተጫራቾች አወዳድሮ ማሰራት ይፈሌጋል፡፡
CMC Sunshine No 2 Village
የሲ.ኤም.ሲ ሰንሻይን ቁ2 የመኖሪያ መንደር የጋራ ህንፃ ቤቶች ከብሎክ 49-114 የቤት ባለቤቶች ማህበር የአፓርትመንቱን መግቢያ በሮች፣ ቡዞች ፣የጥበቃ ቤቶች፣ የሽቦ አጥር እና የማስታወቂያ ቦርድ በጥራት እና በተገቢው የቴክኒክ መስፈርት ብቁ በሆኑ ተጫራቾች አወዳድሮ ማሰራት ይፈሌጋል፡፡
| ተ.ቁ | የሥራ መግለጫ |
| 1 | በር አንድ 80/በ80 በሆኖ ፍሬም ዉስጡ 60/40 እንዲሁም ቲክነሱ 2ሚ በሆነ ብረት እና በሁለቱም ሳይድ ኮለን
ያለዉ ቁመቱ 3.20 ሜትር ስፋቱ 40 በ40 የሆነ እና የእግረኛ በር 3 ሜትር በ 1 በሜትር ያለዉ 70 ሴንቲ ሜትር ወደ ታች ተቀብሮ የሚተከል የተከፋቹ ቁመት 3 ሜትር የሁለቱ በር ተከፋች ስፋት 4.5 ሜትር |
| 2 | በር ሁለት 80/በ80 በሆነ ፍሬም ዉስጡ 60/40 እንዲሁም ቲክነሱ 2ሚ በሆነ ብረት ቁመት 3 ሜትር የሁለቱ
ተከፋች ስፋት 4 ሜትር ኮለኑ በራሱ ሊይ ሆኖ በአንዱ ሳይድ 50 ሴ.ሜ ተጨማሪ ተገንብቶ የሚሰራ እና መግቢያ መዉጫዉ ላይ ራምፕ የሚሰራ |
| 3 | በር ሶስት 40/በ40 በሆነ ፍሬም ዉስጡ 30/20 እንዲሁም ቲክነሱ 2ሚ በሆነ ብረት ቁመት 3 ሜትር የሁለቱ
ተከፋች ስፋት 3.50 ሜትር ኮለኑ ባለበት ሆኖ ትርፉ 1.5 ሜትር ለሁለት ተካፍሎ በሩ ይገጠማል እንዲሁም የእግረኛ በር 1 ሜትር በ ሜትር የሚሰራ |
| 4 | የጥበቃ ቤቶች ብዛት 3 የሚሰሩበት ማቴሪያሌ በ48 ltz ቁመቱ 2.40 ስፋቱ 1.50በ2.25 ከመሬት አንድ ሜትር ወደ
ሊይ በለበር ላሜራ በ4m መስታወት 60በ60 ወደ ዉጭ ተከፋች ከንቹ በማይታይ ጣራዉ በኤጋ ቆርቆሮ በኮንክሪት ሙሌት |
| 5 | የሽቦ አጥሩ በሜሽ ቋሚ ባለ2 RHS ብረት በ 2.5 ሜትር ስፋት ማገሩ 30 በ 20 ጋሌባናይዝድ ሮሌ |
| 6 | የቡዝ ሳይዝ ቁመቱ 2.40 ስፋቱ 1.20በ2ሜትር ኮንክሪት ፕላት ፎርም |
| 7 | የማስታወቂያ ቦርድ 2ሜ በ1.5ሜ የማህበሩ መለያ ፁሁፍ የሚፃፍበት
የሲ.ኤም.ሲ ሰንሻይን ቁ2 የመኖሪያ መንደር የጋራ ህንፃ ቤቶች ከብልክ 49-114 የቤት ባለቤቶች ማህበር |
የጨረታ ተጫራቾች መስፈርቶች
- የሥራ ዋስትና የባንክ ቼክ ማስያዝ የሚችል
- የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለዉ
- ቲን ናምበር ያለዉ
- ንግድ ምዝገባ
- VAT ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል
- ከጨረታ ሰነዱ ጋር የሥራ ልምድ ማቅረብ የሚችል
- ሙሉ ማቴሪያሉን ግቢ ዉስጥ አምጥቶ መሥራት የሚችል
- በ 1 ወር ከ 15 ቀን ሰርቶ ማስረከብ የሚችል
ማሳሰቢ ያ
- ተጫራቾች የጨረታዉን እንቨልፕ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ7 ተከታታይ የሥራ ቀናት ዉስጥ በግቢዉ ዉስጥ በሚገኘዉ የኮሚቴ ቢሮ በአካል ተገኝታችዉ እንድታስገቡ ስንል እናሳስባለን፡፡
- ተጫራቾች የሥራዉ ቦታዉን በመጎብኘት የሥራዉን መጠንና ሁኔታ በማረጋገጥ ዋጋ እንድታቀርቡ እያሳሰብን የሚሰሩትን መግቢያ በሮች፣ ቡዞች ፣የጥበቃ ቤቶች፣ የሽቦ አጥር እና የማስታወቂያ ቦርድ ዲዛይን ኮሚቴ ቢሮ በአካል ቀርባችሁ ማየት አለባችሁ ፡፡
- በተቀመጠዉ መስፈርት ሊሰራ የተስማማዉ ድርጅት ከተወዳዳሪዎች ዝቅተኛ ጨረታ የሚያስገባዉ አሸናፊ ይሆናል፡፡
- ኮሚቴዉ ጨረታዉን በሙሉም ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት ያለዉ መሆኑን እናሳዉቃለን፡፡
