በ2019 በጀት ዓመት ፋብሪካው ግዢ በሚፈጸምባቸው ግብዓቶች፣ የግንባታ ቁሳቁሶች፣ ሸቀጦች፣ መለዋወጫ ዕቃዎች እና ተያያዥ አገልግሎቶችን ለማቅረብ የሚችሉ አቅራቢዎችን በመመዝገብ የወጣ ማስታወቂያ።
የሀገር ውስጥ ጨረታ
ቁጥር ሙሲፋ/24/26/2018
በ2019 በጀት ዓመት ፋብሪካው ግዢ በሚፈጸምባቸው ግብዓቶች፣ የግንባታ ቁሳቁሶች፣ ሸቀጦች፣ መለዋወጫ ዕቃዎች እና ተያያዥ አገልግሎቶችን ለማቅረብ የሚችሉ አቅራቢዎችን በመመዝገብ የወጣ ማስታወቂያ።
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙግር ሲሚንቶ ፋብሪካ በ2019 በጀት ዓመት ፋብሪካው ግዢ ለሚፈጸምባቸው ግብዓቶች፣ የግንባታ ቁሳቁሶች፣ ሸቀጦች፣ መለዋወጫ ዕቃዎች እና ተያያዥ አገልግሎቶችን ለማቅረብ የሚችሉ አቅራቢዎችን በጨረታ አወዳድሮ መመዝገብ ይፈልጋል፡፡
ከፋብሪካው ጋር አብሮ ለመሥራት የሚፈልጉ አቅራቢዎች የማይመለስ ብር 575.00 ከነቫቱ በመክፈል የፍላጎት መግለጫ ሰነዱን አዲስ አበባ በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት ገርጂ አካባቢ የቀድሞው ኢምፔሪያል ሆቴል መዳረሻ ወለል ከሚገኘው የፋብሪካው ግዥ መምሪያ ቢሮ እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የፍላጎት መግለጫ ሰነዳቸውን (መሳተፍ የሚፈልጉበትን የአቅርቦት ዘርፍ የሚገልጽ ደብዳቤ በመጻፍ) ከተጠቀሱት ዶክመንቶች ጋር በማያያዝ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 5 ቀን 2019 ዓ.ም ከረፋዱ 3፡30 ሰዓት ድረስ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ የፍላጎት መግለጫቸውን አዲስ አበባ በሚገኘው በግዥ መምሪያ ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ሰነዱ በዕለቱ መስከረም 5 ቀን 2019 ዓ.ም ተሳታፊዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት በግዥ መምሪያ ቢሮ ይከፈታል፡፡
ፋብሪካው ፍላጎቱን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አዲስ አበባ
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ
