Tender Detail

Tender Details


ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ኢማ የተለያዩ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን፤ ካቦ፤ ፕላስቲክ ገመድ፤ የመኪና መሸፈኛ ሸራ እና የተለያዩ ዎርከ ሾፕ እቃዎችን በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ አ.ማ


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር Gada/NCB/10/2018

 

ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ኢማ የተለያዩ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን፤ ካቦ፤ ፕላስቲክ ገመድ፤ የመኪና መሸፈኛ ሸራ እና የተለያዩ ዎርከ ሾፕ እቃዎችን በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡ በዚሁ መሰረት

1.     በዘርፉ የተሰማሩ ፤የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የታደሰ ንግድ ፍቃድ እንዲሁም ንግድ ምዝገባ ምስከርእና ሌሎች አስፈላጊውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል

2.     ማንኛውም ተወዳዳሪ ተጫራች የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀን አየር ላይ የሚውል ሲሆን ሰንጋ ተራ ንግድ ስራ ኮሌጅ ፊት ለፊት ቢፍቱ አዱኛ ህንጻ 12ኛ ፎቅ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 በመምጣት የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ) ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይችላሉ፡፡

3.     ማንኛውም ተጫራች በገዛው የጨረታ ሰነድ ላይ ከብ ማህተም በማድረግ እና በመፈርም በሰም በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

4.     ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚወዳደሩትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን የሞሉትን ጨረታ ሰነድ ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ሰነድ ኦሪጅናል እና ፎቶ ኮፒ እንዲሁም የስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በተለያዬ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው፡፡

5.     የጨረታ አሸናፊነቱ ከተረጋገጠ ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት የዋጋውን ውል ማስከበሪያ 10 % በማስያዝ ውል መፈረም ይኖርባቸዋል፡፡

6.     ተጫራች በሚያቀርቡት ዋጋ የጨረታ መግቢያ ሰዓት ከተጠናቀቀ በኋላ ማሻሻያ ማድረግ እና እራሳቸውን ከጨረታ ማግለል አይቻልም፡፡

7.     በሌላ ተጫራች ላይ ተንተረሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም

8.     በጨረታ ሰነዱ ላይ የተሰረዘ እና የተደለዘ ሆኖ ለመለየት የሚያስቸግር ዋጋ ተቀባይነት የለውም፡፡

9.     ለተሸናፊ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙትን ገንዘብ ከእሸናፊ ተጫራቾች ጋር ውል እንደተፈጸመ ተመላሽ ይሆናል፡፡

10.                        ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀን አየር ላይ የሚውል ሆኖ በ16ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው እለት 8፡30 ላይ ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡

11.                        የጨረታ መክፈቻ ቀናት ፤ቅዳሜ እና እሁድ እንዲሁም በበዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡

12.                        ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው:: አድራሻ ÷ ሰንጋ ተራ ንግድ ስራ ኮሌጅ ፊት ለፊት ቢፍቱ አዱኛ ህንጻ 7ኛ ፎቅ

ለበለጠ መረጃ ስልከ ቁጥር 011-558-25-19

 

ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ አ.ማ

 

Save Tender