የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
በፍ/ባለሙበት ወ/ሮ አደን ይጥና በቀለ እና በፍ/ባለዕዳ እነ ወ/ሮ ላቀች ተካልኝ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 10838 09/10/2017 ዓ.ም እና በኮ/መ/ቁ 15687 በ20/6/2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በቦሌ ከ/ከተማ ወረዳ 13 የቤ.ቁ 3344 በካርታ ቁጥር ቦሌ03/328/29- 1452/00 ስፋቱ 108 ካ.ሜ የሆነው የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 5,048,468 ( አምስት ሚሊዮን አርባ ስምንት ሺ አራት መቶ ስልሳ ስምንት ብር) ሆኖ የትራንዛከሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሐምሌ 29 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ በ5፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል፡፡፡ ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ C.P.O የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ጽ/ቤት /ስም C.P.O አሠርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንከ በተከፈተ እሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሀራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት
