በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የቤት ሽያጭ የሐራጅ ማስታወቂያ አዉጥቶል።
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
ድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
በፍ/ባለመብት እነ አቶ አጥናፍ ታቼ እና በፍ/ባለዕዳ ወ/ሮ እመቤት መንክር መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ/56277 28/03/2010 ዓ.ም እና በመ/ቁ 102847 023/3/2015ዓ.ም በመ/ቁ 103388 በ15/2/2015 ዓ.ም በመ/ቁ/104308 በ01/06/2015 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 02 የቤት ቁጥር 214 ካርታ ቁጥር አከ-05/18/1/5444/ ኢካርታ በእነ እማማ ጨርቆስ ስም የተመዘገበ አዋሳኞቹ በምዕራብ መንገድ በሰሜን በጂ.አይ.ኤስ መረጃ ላይ ፓርሴል የውስጥ ቤት ቁጥር 210፣ 21፥ 212፣ የተገለጹ ቤቶች በምስራቅ በጂ.አይ.ኤስ መረጃ ላይ ፓርሴል 3 ውስጥ በቤት ቁጥር 189፣191192 የተገለጹ ቤቶች እንዲሁም በጂ.አይ.ኤስ መረጃ ላይ ፓርሴል 4 ውስጥ በቤት ቁጥር 193፣194፣195 በደቡብ በጂ.አይ.ኤስ መረጃ ላይ ፓርሴል 11 ውስጥ በቤት ቁጥር 215፤216፣217 218 219 220፣191 የተገለጹ ቤቶች የሚያዋስኑት ሆኖ የቦታ ስፋት 216.61 ካ/ሜ ቦታው ከጠቅላላው ይዞታ 23.27 ካ/ሜ መንገድ የሚነካው ሆኖ የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 14,658,429.09 (አስራ አራት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሃምሳ ስምንት ሺህ እራት መቶ ሃያ ዘጠኝ ከ09/100) ሆኖ የትራዛከሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ለመሸጥ ቀጠሮ የተያዘ ቢሆንም በዕለቱ ምንም ተጫራች ባለመቅረቡ ምክንያት ጨረታው ሳይከናወን ቀርቷል፡፡ ስለሆነም በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.102847 በ05/10/2018ዓ.ም
ስተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ድጋሚ ሐራጅ ሆኖ 1/4ኛ 3,664,607.27( ሶስት ሚሊዮን ስድስት መቶ ስልሳ አራት ሺህ ስድስት መቶ ሰባት ከ27/100) ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሐምሌ 20 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 5፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው, ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ከፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፤እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚያመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት⁄ ስም C.P.O በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት፤ በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ, ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ስበስጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሱ መሆኑን እንገልጻስን፡፡
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
