Tender Detail

Tender Details


ሕብረት ባንክ አ.ማ. በቅርንጫፉ በኩል ለሰጠው ብድር በመያዣነት የያዘውን እና ከዚህ በታች የተመለከተውን መኖሪያ ቤት በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልጽ ሐራጅ (ጨረታ) አወዳድሮ ይሸጣል፡፡

Hibret Bank


የሐራጅ ማስታወቂያ

ሕብረት ባንክ አ.ማ. በቅርንጫፉ በኩል ለሰጠው ብድር በመያዣነት የያዘውን እና ከዚህ በታች የተመለከተውን መኖሪያ ቤት በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልጽ ሐራጅ (ጨረታ) አወዳድሮ ይሸጣል፡፡

የተበዳሪ ስም
የአስያዥ ስም
አበዳሪው ቅርንጫፍ
ቤቱ የሚገኝበት አድራሻና የቦታ ስፋት
የይዞታ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ቁጥር
የሐራጅ መነሻ   ዋጋ በብር
ሐራጁ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት
አቶ ሙሉሰው እንዳክመው መኮንን

 

አቶ ገ/ትንሳኤ ነርኤ ተስፋዬ

 

የረር ጎሮ
አዲስ አበባ ከተማ፣ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10፣የቦታ ስፋት 250 ካ.ሜ የሆነ አገልግሎቱ ለመኖሪያ የሆነ G+2 (ባለሁለት ፎቅ) ቤት
ቦሌ10/104/1/7/2093/51220/01
30,747,840.00
ነሐሴ 16 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 5፡00 እስከ 6፡00

የሐራጅ ደንቦች፡-

  1. የሐራጁን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ በሕብረት ባንክ አ.ማ.(Hibret Bank C) ስም የተሰራ የባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ.) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡ከባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ) ውጭ የሚቀርብ የጨረታ ማስያዣ ተቀባይነት የለውም፡፡
  2. ለሐራጅ የቀረበውን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች ከቅርንጫፉ ወይም ከሕግ አገልግሎቶች መምሪያ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ ከጨረታው ዕለት ሶስት ቀናት አስቀድሞ መጎብኘት ይችላል፡፡
  3. በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ተበዳሪ እና አስያዥ ብቻ ናቸው፡፡ተጫራቾች በሐራጅ ለመሳተፍ ሲመጡ መታወቂያ መያዝ ይገባቸዋል፡፡ተጫራቾች የሕግ ሰውነት የተሰጣቸው አካላት ከሆኑ ደግሞ ሕጋዊ ሰውነት ያገኙበትን የዋና ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ሐራጁን ለመሳተፍ የቀረበው ሰው ስልጣኑን የሚያሳይ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ፅ/ቤት ወይም በተመሳሳይ አካል የፀደቀ መመስረቻ ፅሁፍ(የመተዳደሪያ ደንብ)፣ቃለ ጉባኤ ወይም የውክልና ሰነድ ይዞ መቅረብ አለበት፡፡
  4. ሐራጁ የሚካሄደው የሕብረት ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት ሕንፃ (ሕብር ታወር) 26ኛ ፎቅ የሕግ አገልግሎት መምሪያ ባለው የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ነው፡፡
  5. የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጁ መዝጊያ ሰዓት ሰላሳ ደቂቃ በፊት ይደረጋል፡፡
  6. ከፍተኛ ዋጋ ላልሰጡ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡ከፍተኛ ዋጋ ለሰጠ ተጫራች ደግሞ ያቀረበውን ዋጋ ባንኩ ሲቀበለው ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ አጠቃልሎ እንዲከፍል የሚገልፅ ደብዳቤ የሚሰጠው ሲሆን በዚህ ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ግን ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል፡፡በተጨማሪም ንብረቱ በድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል፡፡
  7. የጨረታው አሸናፊ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ሌሎች የጨረታ አሸናፊ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎችን ይከፍላል፡፡
  8. ባንኩ ጨረታውን በማንኛውም ጊዜ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  9. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-የረር ጎሮ ቅርንጫፍ፡ 0116 67 72 53 ወይም የሕግ አገልግሎቶች መምሪያ፡ 0114 70 03 15/47 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
Save Tender