Tender Detail

Tender Details

  • Company የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ጎንደር ቅ/ፅ/ቤት
  • Address ጎንደር ከተማ ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251913871445
  • Website
  • Deadline26 Jun 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Securityየሚያቀርቡትን አጠቃላይ ዋጋ 2%
  • opening date2026-06-26 14:00:00
  • Categories Building Materials , Construction Materials And Raw Materials

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ጎንደር ቅ/ፅ/ቤት በአምዋጭ ስደተኛ ሳይት ዳባት ከተማ እና በአፍጥጥ ስደተኛ ሳይት ገንደ ውሃ ከተማ በሚገኘው በስደተኛ ሳይቱ መጋዘን የሚገኘውን ሲሚንቶ ባለበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ጎንደር ቅ/ፅ/ቤት


የሲሚንቶ ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡ ስተአ/ዳባት/001/2018

 

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ጎንደር ቅ/ፅ/ቤት በአምዋጭ ስደተኛ ሳይት ዳባት ከተማ እና በአፍጥጥ ስደተኛ ሳይት ገንደ ውሃ ከተማ በሚገኘው በስደተኛ ሳይቱ መጋዘን የሚገኘውን ሲሚንቶ ባለበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ባወጣው የዕቃዎች ሽያጭ ጨረታ መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች፡-

1)     ተጫራቾች የተዘጋጀውን የሽያጭ ጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል በጎንደር ቅ/ፅ/ቤት እና በአፍጥጥ ስደተኛ ሳይት በሚገኘው የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት መ/ቤት ቅጥር ግቢ አስተዳደርና ፋይናንስ ቢሮ በመገኘት እና ክፍያ በመፈጸም ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ከሰኔ 08 እስከ 19 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 6:30 ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይቻላል፡፡

2)     በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚያቀርቡትን አጠቃላይ ዋጋ 2% ለስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት /Refugees and Returnees Service /በሚል የተዘጋጀ የክፍያ ማዘዣ /CPO/ የባንክ ዋስትና /Bank Gurantee/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

3)     ማንኛውም ተጫራች ከሰኔ 08 እስከ 19 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ጎንደር ቅ/ፅ/ቤት እና ገንደውሃ በሚገኘው የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ቅጥር ግቢ በመገኘት ዕቃዎቹን መመልከት ይችላል። ቅዳሜና እሁድ የስራ ቀናት አይደሉም፡፡

4)     ጨረታው ጎንደር ከተማ አምባራንስ ሆቴል በሚገኘው የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ቅጥር ግቢ የሚካሄድ ሲሆን የጨረታው ሳጥን ሰኔ 19 ከቀኑ 7፡30 ታሽጎ በዕለቱ ከቀኑ 8፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡

5)     የጨረታ አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ያሰያዙት ሲፒኦ ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ያሰያዙት የጨረታ ዋስትና በ3 ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡

6)     ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ወይም በማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎችን መረከብ አለባቸው።

7)     በተራ ቁጥር 6 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረገ ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዘው ሲፒኦ ለአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ገቢ በማድረግ የተሻለውን አማራጭ የመውሰድ መበቱ የተጠበቀ ነው፡፡

8)     አገልግሎት መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

9)     ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር +251913871445 ወይም 251910048505 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ጎንደር ቅ/ፅ/ቤት

Save Tender