Tender Detail

Tender Details

  • Company የኢትዮ ኤሌክትሪክ ስፖርት ክለብ
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011155344949
  • Website
  • Deadline22 Jun 2026, 2:00 PM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Security30,000
  • opening date2026-06-22 14:30:00
  • Categories Transportation Service And Cargo

ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ስፖርት ክለብ ለ2019 በጀት ዓመት የሚሆን የትራንስፖርት አገልግሎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ አገልግሎቱን ማግኘት ይፈልጋል።

የኢትዮ ኤሌክትሪክ ስፖርት ክለብ


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፣-ኢኤስክ/ግጨ-05/2018

 

ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ስፖርት ክለብ ለ2019 በጀት ዓመት የሚሆን የትራንስፖርት አገልግሎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ አገልግሎቱን ማግኘት ይፈልጋል።

ተቁ

 

የዕቃው ዓይነት

 

የጨረታ ማስከበሪያ

 

የጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት

 

የጨረታ መክፈቻ ቀንናሰዓት

 

1

 

የትራንስፖርት አገልግሎት

 

30,000

 

15/10/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት

 

15/10/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት

 

 

ስለሆነም በጨረታው መካፈል የሚፈልግ ድርጅት ወይም ግለሰብ ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

1.    የትራንስፖርት አገልግሎት አቅራቢ ዘርፍ የተሰማሩበት የዘመኑ ግብር የተከፈለበት የንግድ ፈቃድ ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የታደሰ የታከስ ክሊራንስ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል የግብር መለያ ቁጥር ያለው በጨረታ መሳተፍ ይችላል።

2.    ተጫራቾች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት፣ ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ በመደበኛ የስራ ሰዓት የስፖርት ክለቡ ጽ/ቤት በመገኘት መግዛት ይችላሉ።

3.    ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Bid Security) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

4.    ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን እና የጨረታ ማስከበሪያቸውን ስማቸውን እና ጨረታ ቁጥሩን በመግለፅ ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ድረስ ብቻ በተጠቀሰው አድራሻ ብሔራዊ ቲያትር አካባቢ ናይል ኢንሹራንስ 10ኛ ፎቅ በሚገኘው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ስፖርት ክለብ ጽ/ቤት ማስገባት አለባቸው።

5.    ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻው በተገኙበት ብሔራዊ ቲያትር አካባቢ ናይል ኢንሹራንስ 10ኛ ፎቅ በሚገኘው ስፖርት ክለቡ ጽ/ቤት ይከፈታል።

6.    ስፖርት ክለብ ለሚፈጽመው ለስፖርተኞች አገልግሎት የሚሆን የትራንስፖርት አገልግሎት የፋይናንስ ሰነዳቸውን በተለያየ ኤንቨሎፕ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው። በተጨማሪ ለሚወዳደሩበት ማቅረብ ይገባቸዋል።

7.    ጨረታው የሚከናወነው በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ሥነ-ሥርዓት መሆንኑ አስመልክቶ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ስፖርት ክለብ መመሪያ መሠረት ሲሆን ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ የሚገልፅ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የግብር ከፋይ ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን ይኖርበታል።

8.    ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

9.    በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተተርሶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው፤

10.        ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር፡- 011-1-55-34-49-49 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

 

 የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ስፖርት ክለብ

Save Tender