አማራ ክልል ግብርና ቢሮ የደረቅ ጭነት መኪና ኪራይ (የግብርና ምርት ለማጓጓዝ) አገልግሎቱን ማቅረብ ከሚችሉ ተጫራቾች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ግዥ ፈጻሚው መስሪያ ቤት፡ የአማራ ክልል የግብርና ቢሮ
የፕሮጀክቱ ስም፡ የአየር ንብረት የማይበገር የስንዴ እሴት ሰንሰለት ልማት (CREW) ፕሮጀክት
የግዥው መለያ ቁጥር፡ ET-CREW-AMHARA-1/2026-NCS-OCB_N
የሚገዛው አገልግሎት ዓይነት፡ የደረቅ ጭነት መኪና ኪራይ (የግብርና ምርት ማጓጓዝ)
የጨረታ ሰነዱ የወጣበት ቀን፡ ሚያዝያ 05/2018 ዓ.ም (ሚያዝያ 04/2018)
ቢሮው በ CREW ፕሮጀክት የግብርና ሥራው ከአማራ ክልል ምሥራቅ ጎጃም ዞን ደጀን ከተማ አጠገብ ከሚገኝ ፋብሪካ 41,000 ኩንታል የግብርና ምርት ግዥ መፈጸሙ ይታወቃል። በመሆኑም ከፋብሪካው ወደ ተለያዩ የዞን እና የወረዳ ከተሞች የግብርና ምርት ለማጓጓዝ የአገልግሎት ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል።
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
1. በዘርፉ የተሰማራ እና በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፤
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፤
3. የደረቅ ጭነት መኪናውን ሊብሬ ኮፒ እና ሌሎች ተያያዥ ሰነዶች ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከአርጅናል ጋር በማመሳከር ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
1. የግብርና ምርት የሚጓጓዙበት የዞን እና የወረዳ ከተሞች መድረሻ (ማውረጃ ቦታ) ዝርዝር መግለጫ እና መቅረብ ያለባቸው አስፈላጊ መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 1,000 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል ቢሮ ቁጥር 20 ማግኘት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች ለአገልግሎት ግዥው (ለመኪና ኪራይ) ለሁሉም ሎቶች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ (unconditional Bank Guarantee) ብቻ ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። [lnsert Blue Stamp lmage Here]
ማንኛውም ተጫራች የጨረታ የመወዳደሪያ ሃሳቡን የቴክኒክ ሰነድ ዋና እና የፋይናንስ ሰነዱን እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ግብርና ቢሮ ቢሮ ቁጥር 64 ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 12 ተከታታይ ቀናት እስከ 4:00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
ጨረታው የሚከፈተውም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግብርና ቢሮ ስብሰባ አዳራሽ ይሆናል። የመክፈቻው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን 4:00 ታሽጎ 4:30 ይከፈታል።
መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 64 ድረስ በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 58 53 / 09 18 08 49 61 / 09 11 35 79 49 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
ተጫራቾች ያለምንም ስርዝ ድልዝ የተሞላ ዋጋ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ሆኖም አስገዳጅ ሁኔታ ሲገጥም ከተሰረዘው ላይ የሞላው ድርጅት ፊርማ መኖር አለበት።
በዚህ የጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ህጎችና ደንቦች በፌዴራል መንግስት የግዥ መመሪያው መሰረት ተፈጻሚ ይሆናሉ።
አማራ ክልል ግብርና ቢሮ
